ይህ ጽሑፍ በመጠኑም ቢሆን ስለገብረ ክርስቶስ ደስታ ማንነት የሚያትት ሆኖ ስላገኘሁት የዶክተር ፍቃደ አዘዘን ንግግር በፎቶ መልክ ገጼ ላይ ለጥፌዋለሁ፡፡ርግጥ ውይይቱ የተካሄደው የዛሬ አስር ዓመት ገደማ ቢሆንም ቅሉ ፣ ካለው ኪነጥበባዊ ፋይዳ አንጻር ለአጥኚዎች እንደ አንድ ግብዓት ማገልገሉ እሙን ነው፡፡ ውድ የእልፍኜ ታዳሚያን ፣ በገጣሚና ሰዓሊ ገብረ ክርስቶስ ደስታ ሥራዎች እና የሕይወት ጉዞ ላይ ተጨማሪ መረጃ ካላችሁ በኢሜል አድራሻዬ ትልኩልኝ ዘንድ መልካም ፍቃዳችሁን እለምናለሁ፡፡
ልጥፎችን በመለያ ፈርጦቹ በማሳየት ላይ። ሁሉንም ልጥፎች አሳይ
ልጥፎችን በመለያ ፈርጦቹ በማሳየት ላይ። ሁሉንም ልጥፎች አሳይ
ረቡዕ 16 ኦክቶበር 2013
ዓርብ 16 ኦገስት 2013
መርፌ ትሠራለህ? - ያልተፈታው ቅኔ (በ ግሱ)
መርፌ ትሠራለህ? -
ያልተፈታው ቅኔ (በ ግሱ)
ስለአብዬ መንግሥቱ ቅኔ ሙያዊ
ዳሰሳ ለአንባቢዎቼ እንዳካፍል በማሰብ ይህን ጽሑፍ ላደረስከን (ግሱ) ልባዊ ምስጋናዬ ይድረስህ፡፡ ውድ የእልፍኜ ተከታታዮች እና
አንባቢያን ሙሉ ጽሁፉ በ ፒዲኤፍ ፋይል ከዚህ በታች ያገኙታል፡፡ መልካም ንባብ፡፡
ኄ.ስ
![]() |
| merefe teseraleh? |
ሰኞ 17 ጁን 2013
ሰኞ 27 ሜይ 2013
የትም የተፈጨ ዱቄት አንበላም - ታሪካዊ ደብዳቤ - በፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም
.....“የትም ፍጭው፣ ዱቄቱን አምጭው” የሚሉ አይጠፉም፡፡ ግን ዱቄቱ የሚፈጭበት መጅና
ወፍጮ ንፅህና፣ የሚፈጭበት ቤት ነዋሪዎች ጤንነት፣ ..... የእንጀራውን ጣእምና ተበይነት
ይወስነዋል፡፡ ህይወት የትም የተፈጨ ዱቄት የሚበላበት ዘመን አይደለም፡፡ ያልፈጩትን እህል ከውርደት ጋር በልቶ ከመኖር በረሃብ
መሞት ይሻላል፡፡ በኩራት ኖሮ፣ በኩራት ካልተሞተ ህይወት ሌላ ምን ትርጉም አለው?
በ1995 አእ የስዊስ መንግስት 10ሺ ዶላር ለኢሰመጉ ከሰጠ በኋላ፣ በገንዘቡ ዋጋ
ኢሰመጉን መግዛት የሚችል መስሎት፣ “ኢሰመጉ ባወጣው ዘገባ መንግስትን ያለአግባቡ ነቅፏል” በማለት ኢሰመጉን አወገዘ፡፡ በጊዜው
የኢሰመጉ ሊቀመንበር የነበሩት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም የሚከተለውን ደብዳቤ ለስዊሱ አምባሳደር ጻፉለት፡፡ ደብዳቤው
የተጻፈው በእንግሊዘኛ ነበር፡፡ ግን የተጠቀሰውን የሼሊን ውብ ግጥም በአማርኛ ማንበብ ስለፈለግሁ ደብዳቤውን በሙሉ ወደ አማርኛ
ተርጉሜዋለሁ፣ ለሚገኘው የትርጉም ስህተት አስቀድሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡
ይህ ታሪካዊ ደብዳቤ፣ ኢትዮጵያውያን የትም የተፈጨ ዱቄት እንደማንበላ በግልፅ
የሚያሳይ ነውና ህፃናትም በቃላቸው ሊያጠኑት ይገባል፡፡
ኦክቶበር
9. 1995
ለክቡር
ዶክተር ፒተር አ.ሽዋይዘር
የስዊዘርላንድ
አምባሳደር
አዲስ
አበባ፣ ኢትዮጵያ
ክቡር
ሆይ
ምናልባት፣
(ደብዳቤዬን) በሼሊ “የፍቅር ሽሽት” መጀመሩ ተገቢ ሳይሆን አይቀርም፡፡
ፋኖሱ
ሲተረከክ
የአቧራ ላይ ብርሃን ያከትማል
ደመናው
ሲበተን
የቀስተ ደመናው ግርማ ይነጥፋል
ዋሽንቱ
ሲሰበር
ጣፋጭ ድምፆች ይተናሉ
ከንፈሮች
ተናግረው ሲያበቁም
የፍቅር ቃናዎች ይረሳሉ፡፡
ከአምባሰደሮች ሁሉ የላቁ የኢሰመጉ ወዳጅ እንደነበሩ አለመርሳታችንን (በቅድሚያ)
ላረጋግጥልዎ እወዳለሁ፡፡ ቀደም ሲል የሞራል ድጋፍ እንዳደረጉልንም አልረሳንም፡፡ ለዚያም ውለታው አለብን፡፡
ከኢሰመጉ ጋር ያለዎት የቅርብ ግንኙነት ሳይሆን አይቀርም የትስስሩ ጥንካሬ በዚህ
አጋጣሚ ለፈተና የተጋለጠው፡፡ ትስስሩም ደካማ መሆኑ በግልጽ ታወቀ፤ እንዲያም ሆኖ የመታውን ማእበል መቋቋም ተሳነው፡፡ ለመርህ
የነበረንን አክብሮት ትተን በነበረን የጋራ ስሜት ምን ያህል መልካም እንደሠራን መገንዘቡ ከኛ ይልቅ ለክቡርነትዎ ግልፅ ነው፡፡
ክቡርነትዎ 10000 ዶላር የሚገመት ሃብት የማባከን ስሜት እንደተጫጫነዎ ያስታውቃል፡፡ ለዚህም የብክነት ስሜትዎ ማካካሻ
ብሄራዊ ራታችንን፣ ሰብአዊ ክብራችንን እና ለመርህ ያለንን ተገዥነት እንድንሸጥልዎ ያደረጉት ሙከራ ምን ያህል እንዳስቆጣን
ክቡርነትዎ ሊገነዘበው ይገባል፡፡ እንደ ሸክስፒር አባባል፣ ጣፋጭ ነገሮች በምግባራቸው ወደ ኮምጣጣነት ይቀየራሉ፡፡
በመንፈስ ደሃ እንዳልሆንን ክቡርነትዎ አይጠራጠሩም፡፡ ገንዘብዎን ለመመለስ ረዥም
ጊዜ ስለወሰደብንም ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ውግዘት ከኢሰመጉ የባንክ መዝገብ ህገወጥ እገዳ ጋር ተጣምሮ መምጣቱን ክቡርነትዎ
ያውቀዋልና፡፡ ሆኖም፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ከኢሰመጉ ጎን በመሰለፍ ገንዘቡን በሙሉ እንድከፍል ስላስቻለን ደስ ብሎናል፡፡ ቼኩን
ከዚህ ደብዳቤ ጋር አያይዘን ልከናል፡፡
ከመልካም ምኞት ጋር
አክባሪዎ
መስፍን ወልደ ማርያም
የኢሰመጉ ሊቀመንበር
--------
አምሃ አስፋው በገብረክርስቶስ ደስታ ግጥሞች (መንገድ ስጡኝ ሰፊ) ላይ ካቀረቡት ዳሰሳ
ላይ ከ”አንድምታ መጽሔት” የተቀነጨበ /1999ዓ.ም/
ዓርብ 3 ሜይ 2013
ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት /ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን/
ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት
/ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን/
------------
አዬ፣ ምነው እመ ብርሃን? ኢትዮጵያን ጨከንሽባት?
ምነው ቀኝሽን ረሳሻት?
እስከመቼ ድረስ እንዲህ፣ መቀነትሽን ታጠብቂባት?
ልቦናሽን ታዞሪባት?
ፈተናዋን፣ ሰቀቀኗን፣ ጣሯን ይበቃል ሳትያት?
አላንቺእኮ ማንም የላት….
አውሮጳ እንዲሁ ትናጋዋን፣ በፋሽስታዊ ነቀርሳ
ታርሳ፣ ተምሳ፣ በስብሳ
ሂትለራዊ እባጭ ጫንቃዋን፣ እንደኮረብታ ተጭኗት
ቀና ብላ እውነት እንዳታይ፣ አንገቷን ቁልቁል ጠምዝዟት
ነፍሷን ድጦ ያስበረከካት
ሥልጡን፣ ብኩን፣ መፃጉዕ ናት፤ ….
እና ፈርቼ እንዳልባክን፣ ሲርቀኝ የኃይልሽ ውጋገን
አንቺ ካጠገቤ አትራቂ፣ በርታ በይኝ እመ ብርሃን
ቃል ኪዳኔን እንዳልረሳት፣ እንዳልዘነጋት ኢትዮጵያን፡፡
አዎን፣ ብቻዬን ነኝ ፈራሁ
እሸሸግበት ጥግ አጣሁ
እምፀናበት ልብ አጣሁ
እማማ ኢትዮጵያን መንፈሴ፣ ተፈትቶ እንዳይከዳት ሠጋሁ …
አዋጅ፣ የምሥራች ብዬ፣ የትብት ምግቤን ገድፌ
ከእናቴ ማኅፀን አርፌ
ከአፈርዋ አጥንቴን ቀፍፌ
ደሜን ከደሟ አጠንፍፌ
ከወዟ ወዜን ቀፍፌ
በሕፃ እግሬ ድሄባት፣ በህልም አክናፌ ከንፌ
እረኝነቴን በሰብሏ፣ በምድሯ ላብ አሳልፌ
ከጫጩት እና ከጥጃ፣ ከግልገል ጋር ተቃቅፌ፤
በጋው የእረኛ አደባባይ፣ ክረምት እንደወንዙ ፍሳሽ
በገጠር የደመና ዳስ፣ በገደል ሸለቆ አዳራሽ
ከቆቅ እና ከሚዳቋ፣ ከዥግራ ጠረን ስተሸሽ
በወንዝ አፋፍ ሐረግ ዝላይ፣ መወርወር መንጠልጠል ጢሎሽ
ከፍልፈል ጋር ሩጫ ስገጥም፣ ከቀበሮ ድብብቆሽ
ከናዳ ጫፍ ሣር አጨዳ፣ ለግት ላሜ ትንሽ ግጦሽ
ለጥጃዬ የሌት ግርዶሽ
ለጥማድ በሬዎች ራት፣ ለማታቸው ትንሽ ድርቆሽ
ለግልገሌ ካውሬ ከለል
እማሳው ሥር ጎጆ መትከል
ለፀሐይ የሾላ ጠለል፣ ለዝናብ የገሳ ጠለል
ውሎ የንብ ቀፎ ማሰስ፣ ያበባ እምቡጥ ሲፈነዳ
የግጦሽ ሣር ሲለመልም፣ ሲሰማሩ ሰደድ ሜዳ
አዝመራው ጣል ከንበል ሲል፣ ከብቱ ለሆራ ሲነዳ
ፈረስ ግልቢያ ስሸመጥጥ፣ ከወፎች ዜማ ስቀዳ
ልቤ በንፋስ ተንሳፎ፣ በዋሽንት ዋይታ ሲከዳ …..
ያቺን ነው ኢትዮጵያ የምላት
እመ ብርሃን እረሳሻት?
/ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን/
------------
አዬ፣ ምነው እመ ብርሃን? ኢትዮጵያን ጨከንሽባት?
ምነው ቀኝሽን ረሳሻት?
እስከመቼ ድረስ እንዲህ፣ መቀነትሽን ታጠብቂባት?
ልቦናሽን ታዞሪባት?
ፈተናዋን፣ ሰቀቀኗን፣ ጣሯን ይበቃል ሳትያት?
አላንቺእኮ ማንም የላት….
አውሮጳ እንዲሁ ትናጋዋን፣ በፋሽስታዊ ነቀርሳ
ታርሳ፣ ተምሳ፣ በስብሳ
ሂትለራዊ እባጭ ጫንቃዋን፣ እንደኮረብታ ተጭኗት
ቀና ብላ እውነት እንዳታይ፣ አንገቷን ቁልቁል ጠምዝዟት
ነፍሷን ድጦ ያስበረከካት
ሥልጡን፣ ብኩን፣ መፃጉዕ ናት፤ ….
እና ፈርቼ እንዳልባክን፣ ሲርቀኝ የኃይልሽ ውጋገን
አንቺ ካጠገቤ አትራቂ፣ በርታ በይኝ እመ ብርሃን
ቃል ኪዳኔን እንዳልረሳት፣ እንዳልዘነጋት ኢትዮጵያን፡፡
አዎን፣ ብቻዬን ነኝ ፈራሁ
እሸሸግበት ጥግ አጣሁ
እምፀናበት ልብ አጣሁ
እማማ ኢትዮጵያን መንፈሴ፣ ተፈትቶ እንዳይከዳት ሠጋሁ …
አዋጅ፣ የምሥራች ብዬ፣ የትብት ምግቤን ገድፌ
ከእናቴ ማኅፀን አርፌ
ከአፈርዋ አጥንቴን ቀፍፌ
ደሜን ከደሟ አጠንፍፌ
ከወዟ ወዜን ቀፍፌ
በሕፃ እግሬ ድሄባት፣ በህልም አክናፌ ከንፌ
እረኝነቴን በሰብሏ፣ በምድሯ ላብ አሳልፌ
ከጫጩት እና ከጥጃ፣ ከግልገል ጋር ተቃቅፌ፤
በጋው የእረኛ አደባባይ፣ ክረምት እንደወንዙ ፍሳሽ
በገጠር የደመና ዳስ፣ በገደል ሸለቆ አዳራሽ
ከቆቅ እና ከሚዳቋ፣ ከዥግራ ጠረን ስተሸሽ
በወንዝ አፋፍ ሐረግ ዝላይ፣ መወርወር መንጠልጠል ጢሎሽ
ከፍልፈል ጋር ሩጫ ስገጥም፣ ከቀበሮ ድብብቆሽ
ከናዳ ጫፍ ሣር አጨዳ፣ ለግት ላሜ ትንሽ ግጦሽ
ለጥጃዬ የሌት ግርዶሽ
ለጥማድ በሬዎች ራት፣ ለማታቸው ትንሽ ድርቆሽ
ለግልገሌ ካውሬ ከለል
እማሳው ሥር ጎጆ መትከል
ለፀሐይ የሾላ ጠለል፣ ለዝናብ የገሳ ጠለል
ውሎ የንብ ቀፎ ማሰስ፣ ያበባ እምቡጥ ሲፈነዳ
የግጦሽ ሣር ሲለመልም፣ ሲሰማሩ ሰደድ ሜዳ
አዝመራው ጣል ከንበል ሲል፣ ከብቱ ለሆራ ሲነዳ
ፈረስ ግልቢያ ስሸመጥጥ፣ ከወፎች ዜማ ስቀዳ
ልቤ በንፋስ ተንሳፎ፣ በዋሽንት ዋይታ ሲከዳ …..
ያቺን ነው ኢትዮጵያ የምላት
እመ ብርሃን እረሳሻት?
እሑድ 24 ፌብሩዋሪ 2013
እንዳይነግርህ አንዳች እውነት ! - ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን
እንዳይነግርህ
አንዳች እውነት ! - ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን
ደንስ ጎበዝ ! ደንስ
ጀግና
ክራቫትህን አውልቅና
ሃሳብህን ልቀቀውና
ኮትክን ሸሚዝክን ጣልና
ርገጥ ፣ ጨፍር ፣ ደንስ
ጀግና !
ያን የሙዚቃህን ናዳ
፣ የኮንትራባሱን መብረቅ
ልቀቀውና ይድብለቅለቅ
ምድር በሆይታ ይጥለቅለቅ
!
ምንም-ምንም እንዳታስብ
፣ ሁሉን-ሁሉን እንድትረሳ
ደንስ ! ካካታው ይነሳ
ጨፍር ፣ ወለሉ እስኪበሳ
....
ሃይ-ሃይ ! ዋይ !
ሃይ-ሃይ ! በልበት
የጃዝ ፋንፋር አንኳኳበት
ራስክን እንዳታስብበት
፤
ሆ ! በል እሪ ! በል
ምታበት
ፎክርበት ፣ አቅራራበት
አናፋበት ፣ ሸልልበት
የሲቃ ሳቅ አስካካበት
ሆያ-ሆዬ ! በል ጩኽበት
ኡኡታህ መንኮራኩርክን
፣ እስኪያሰጥመው አጓራበት
ጭንቅላትክን ግዘፍበት
፣ ውቀጥበት ፣ ውገርበት ፣ ....
ዝግ ብሎማ ያሰበ እንደሁ
፣ ይነግርሃል አንዳች እውነት !
-----------
ባለቅኔ
ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን
እሑድ 10 ፌብሩዋሪ 2013
እውነት አሁን አንቺ እሷ ነሽ! ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን
እውነት አሁን አንቺ እሷ ነሽ! ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ
ገብረ መድኅን
---------
እሷ ነኝ በዪኝ ግድ የለም!
. . . .
ሁሉ ላፍ አልተፈጠረም
ቢሉም አፍ አይለው የለም።
ልወቀውና ላውጣ እርሜን፥
የስንት ዘመን ረሃቤን
ልጋረጠው በዓይንሽ አይኔን።
ልጅነቴን የዳኽኩበት፥ የስንት
ዘመን ፈለጌ
በናፍቆት ቋት ተሰግስጌ
በእግረ ሕሊና ጠርጌ
በትዝታ በዳሰሳ፥ በፈለግሽ የናዳ
ዳር
ስዋትት ስማስን በጣር
ዛሬ ያገኘሁሽ ባሣር
በስንት ዘመን የዕድሜ ምጥ
እውነት አንቺ እሷ ነሽ እርግጥ?!
መምሰል ትመስያለሽ
ማከልማ ታክያለሽ
የደም ግባቷን ተላብሰሽ
መጠሪያዋን ተሰይመሽ . . . .
ያቺን የኔን .... ያቺን የኔን
የኔን የመጀመሪያዬን
የጥንቴን የልጅነቴን
የስንት ዘመን ሕመሜን
የሕልም ዓለም ሰመመኔን
የት አረግሻት? የት ደበቅሻት?
ዋጥሻት? . . . .
አጥንቷን በአጥንትሽ ለብሰሽ
ወዟን በላቦትሽ ታጥነሽ
በልጅነቷ ልጅ ሆነሽ
ገጿን በግንባርሽ ነድፈሽ
አበቧን አደብዝዘሽ
መልኳን በመልክሽ አክስለሽ
ቡቃያዋን በዕድሜሽ ውጠሽ
በስም ብቻ እሷን ሆነሽ
ማነሽ? እውነት አንቺ ማነሽ
እኮ ንገሪኝ እሷ ነሽ?
እሑድ 27 ጃንዋሪ 2013
የቴዎድሮስ ስንብት ከመቅደላ - ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን
የቴዎድሮስ ስንብት ከመቅደላ
ተስፋ ባጣ ምድረ በዳያንድ እውነት ይሆናል ዕዳ፡፡
እና ትንፋሼ አልሆነሽም፥ ሆኜብሽ መራር መካሪ
“ሩቅ አሳቢ ቅርብ አዳሪ፣”
እውነት ላንቺ መች ተስፋ ናት፥ ጉስቁል ልሳንሽን ነክሳሽ
ክንድሽን ካዘለ ቅርስሽ፥ መጠላለፍ ሲሆን እጣሽ
ከእንግሊዝ የሞት አማልክት፥ መተናነቅ ሲሆን ድርሻሽ
መልመጥመጡ፥ መሽቆጥቆጡ፥ መስሎሽ ድንገት የሚያዋጣሽ
የኔ እውነት ሆነብሽ ዕዳሽ ፡፡ …..
ወራሪም ፈጣሪን ላያቅ
የጣለውን በስሏል እንጂ፥ ወድቋል ብሎ ግፉ ላያልቅ
መች ትተርፊያለሽ ኢትዮጵያ፥ ሕዋስሽ አብሮኝ ካልሠራ
አንገትሽ ብቻ መቅደላ፥ አፋፍ ወጥታ ብታበራ
የቀረው ሠራ-አከላትሽ፥ በየጥሻው ተዘርሮ
ከአባት በወረሽው ንፍገት፥ ነብዞ ደንዝዞ ተቀብሮ
ባጉል ወጌሻ ታጅሎ
እጅና እግርሽ ታሽቶ ዝሎ
እኔን ለጥንብ አንሳ ጥሎ፤
ከደቀቀ ከደከመ፥ ክንድሽ አልነሣ ካለ
ሞት እንጂ ለኔስ ምን አለ?.....
ሆኖም ጐስቋላ አልምሰልሽ፥ የሚያዝንልኝ አልፈልግም
ጠላትሽን በክንድሽ እንጂ፥ በእንባሽ ወዝ ባላሸንፍም
የልቤን ፍቅር በሰተቀር፥ እማወርስሽም ውል የለኝ
የኮሶ ሻጭ ልጅ ደሃ ነኝ፡፡ …..
ሐሙስ 17 ጃንዋሪ 2013
እኔ እወድሻለሁ /ገብረክርስቶስ ደስታ /
እሑድ 13 ጃንዋሪ 2013
ቅዳሜ 12 ጃንዋሪ 2013
ወንድ ብቻውን ነው እሚያለቅስ- ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን

ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ
ተሸሽጎ ተገልሎ፥ ተሸማቆ ተሸምቆ
ከቤተ-ሰው ተደብቆ
መሽቶ፥ የማታ ማታ ነው፥ ሌት ነው የወንድ ልጅ እንባው
ብቻውን ነው የሚፈታው፡፡ . . .
ብቻውን ነው የሚረታው፡፡ . . .
ችሎ፥ ውጦ፥ ተጨብጦ፥ ተማምጦ ተጣጥሮ
በሲቃ ግት ተወጥሮ
እንደደመና ተቋጥሮ
እውስጥ አንጀቱ ተቀብሮ . . .
መሽቶ፥ ረፍዶ፥ ጀምበር ጠልቆ
የጨለማ ድባብ ወድቆ
በእንቅልፍ ጥላ ሲከበብ፥ በዝምታ ሲዋጥ አገር
ፍጡር ሁሉ ተስለምልሞ፥ ብቸኝነት ብቻ ሲቀር . . .
Labels:
ቅኔ,
ፈርጦቹ,
poem,
poetry book,
Tsegaye G/Medhin
ሐሙስ 10 ጃንዋሪ 2013
እግር እንይ! (ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን)
poem in pdf እግር እንይ!(ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን)አርቀን ማስተዋል ማለት፣ የኛን ሥልጣኔ ድልድይእግር ማየት ነው ብለዋል፣ እስቲ እንግዲህ እግር እንይ!ያባቶችህ ያይን ድንበር፣ ከተረከዘ ሎሚ ሳያልፍአንተ ግን ጆቢራው-ዘራፍጠፍር አይወስንህ ጉብልጥሎ በዘመንህ ዕድልዓይንህ ባት አልፎ እንዲዋልል፤ቴህ ወዲያ ጀግንነት የለ፣ ተዚህ የከረረ ግዳጅባደባባይ የዱር ገደል፣ ስትናደፍ የእግር አዋጅሌሊቱን በየሌት- ‘ግለብ’፣ ቀኑን ጭምር በጠራራ
ሰኞ 7 ጃንዋሪ 2013
አደፍርስ - የብዕር ጠብታ /ከባለፈው የቀጠለ/
| ሙሉውን ለማንበብ |
አደፍርስ - የብዕር ጠብታ
(ከባለፈው የቀጠለ)
ቅንጣቢ ዳሰሳ
፡-ሄኖክ ስጦታው
******
****** ****** *****
አደፍርስ የብዕር ጠብታ ነው፡፡ የጥበብ መታያ - የእውነት መገለጫ ነው፡፡ ድብቅ
ሰብእና የለውም፡፡ የገፀ-ባህሪው ውስጠ ምስል ግልፅነት የተከተለ ነው፡፡ የአገራችን ደራሲያን ለዋና ገፀባህሪይ ነፃነት ለመስጠት
የሚጠቀሙበት ተመሳሳይ የአሳሳል ስልት በአደፍርስ ላይ መስተወሉን ልብ ይለዋል፡፡
ዳኛቸው ወርቁ ለአደፍርስ እንደልቡ የመናገር ነፃነትን በመስጠት፣ የራሱን ነፃነት
እንዳወጀ እናስተውላለን፡፡ እውነታውም ይህ ነበር፡፡ የወቅቱን ስርአት፣ ስርአቱ ለዘመናት የፈጠረውን ተፅዕኖ፣ ጭቆና እና ብዝበዛ
ብሎም አጉል ልማዶችን በአደፍርስ አማከኝነት አውግዟል፡፡ በደራሲው ውስጥ አደፍርስ አለ፤ በአደፍርስ ውስጠም ደራሲው ፡፡
መጽሐፉ፣ በተማረው እና ባልተማረው ማህበረሰብ መሀል ለውን ለውጥ ያሳያል፡፡ ስለመሀይምነት
መጥፋት ያትታል፡፡ አደፍርስ ለኢትዮጵያ ያለውን ብሩህ ተስፋ ትምህርትን
አስታኮ ይናገራል፡፡ መዕራፍ 26 ለዚህ ዋቢ የሚሆን ነው፡፡ የምዕራፉ ውይይት አደፍርስ በመጨረሻዎቹ ምዕራፍ ለያዘው ሥራ መጠቆሚያም
ጭምር ሆኗል፡፡
“ሀዲስ” እና “አደፍርስ”
አደፍርስ በዓሉ ግርማ የደረሰው “ሀዲስ” ረጅም ልብ ወለድ ዋና ገፀ ባህርይ ሀዲስ ላይም የባህርይ
ተፅዕኖ ያሳደረ
ረቡዕ 2 ጃንዋሪ 2013
አደፍርስ - የብዕር ጠብታ
| ሙሉውን ለማንበብ |
ርዕስ - "አደፍርስ"
ደራሲ - ዳኛቸው ወርቁ
የታተመበት ዘመን ፲፱፻፷፪ ዓ.ም
ቅንጣቢ ዳሰሳ - በሔኖክ ሥጦታው
ደራሲና ጋዜጠኛ ዘነበ ወላ ባስነበበን መዝገበ-ስብሐት “ማስታወሻ”
መጽሐፍ ላይ ጋሼ ስብሐትን እንዲህ ሲል ጠየቀው፡- “በአንተ የወጣትነት
ጊዜ በአማርኛ ሃሳብን መግለፅ አይቻልም ብላችሁ አንተም ሆንክ ጓደኞችህ በእንግሊዝኛ መጻፍ የወሰናችሁበት ወቅት እንደነበረ ይነገራል።
በኋላ ደግሞ ወደ አማርኛው ተመልሰህ ድንቅ ጸሐፊ ወጣህ። ይህ እንዴት ሊሆን እንደቻለ ብትገልፅልኝ?”
ስብሐት ገብረእግዚአብሔር፦ “በወጣትነቴ አማርኛ በምፈልገው
መልኩ ሀሳብን መግለፅ አያስችልም የሚል እምነት ነበረኝ። በዚህም ላይ ያስተማሩን እንግሊዝኛ ተናጋሪዎች መሆናቸውን አትርሣ። እኛ
አናውቅም እንጂ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ወጣቱን ትውልድ በቅኝ አገዛዝ ጥበባቸው ይዘውናል። በኋላ ዳኛቸው ወርቁ “አደፍርስን” ጻፈ።
እኔ ሳነበው በአማርኛ መጻፍ እንደሚቻል ገባኝ። ስለዚህ በእንግሊዝኛ የመጻፍ ሀሳቤን ተውኩት። በወቅቱ አስታውሳለሁ “ሌቱም አይነጋልኝን”
በእንግሊዘኛ መጻፍ ጀምሬው ነበር። . . .”
ማስታወሻ (ስብሐት ገብረእግዚአብሔር)ከዘነበ ወላ ፤
1993 ዓ.ም የታተመ፤ ገጽ 238
****** ****** ****** *****
“ዳኛቸው ወርቁ «አደፍርስ» (፲፱፻፷፪ ዓ.ም.) በተሰኘ ልብ
ወለድ ድርሰቱ. . . .ጭብጦች እና የተራቀቀ የአጻጻፍ ስልቱ የአማርኛን ዘመናዊ ልብ ወለድ ወደ ድንቅ ከፍ ካለ እርከን ያወጣ፥ «እምቧ በሉ ሰዎች» በሚለው የግጥም መድብሉ
(፲፱፻፷፯ ዓ.ም.) ውስጥ
በተካተቱ ግጥሞቹ ስለሀገሩ ልማትና ዕድገት ተቆርቋሪነቱን የገለጠ ዕውቅ የሥነ ጽሑፍ ምሁር፥ ሐያሲና ተርጓሚ የነበረ ሲሆን በልሳነ
እንግልጣር(እንግሊዝኛ) በመጻፍም «The Thirteenth Sun» የኢትዮጵያን ሥነ ጽሑፍ በዓለም አቀፉ መድረክ
ካስተዋወቁ በጣት ከሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጸሓፍት አንዱ ነበር።” ይለዋል የአማርኛው ዊኪ
ፒዲያ፡፡ሲቀጥልም፡-
“የፊውዳል ኢትዮጵያን ሶሲዮሎጂና የታሪክ ጥራዞች ከማንበብ፥ «አደፍርስ» ድርሰቱን ማንበብ ይቀላል’ የተባለለት ዳኛቸው ወርቁ የካቲት ፲፮ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ.ም. በሰሜን ሸዋ በይፋትና ጥሙጋ በደብረ ሲናከተማ አቅራቢያ ከአቶ ወርቁ በዛብህና ከወይዘሮ አሰገደች ሀብተወልድ ተወለደ። ከቤተ ሰቡ አምሥት ልጆች ዳኛቸው በኩር ነበር።…
የዛሬዎቹን ወጣት ኢትዮጵያውያን በጥበቡ ዘርፍ የሚታደጉ የሥነ ጽሑፍ ጥበብ መመሪያ፣ የአማርኛ ፈሊጦች መጽሐፍት ያሳተመ ምሁር ሲሆን አንድም ለሀገሪቱ ቋንቋ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያላቸውን «የማርክሲዝም ሌኒንዝም መዝገበ ቃላት» እና «የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላት» የመሳሰሉ ጥልቅ እና ምጡቅ ሥራዎች ዝግጅት ላይ በመሳተፍ ምሁራዊ ግዴታውን የተወጣ ኢትዮጵያዊ ነበር።
ሰኞ 31 ዲሴምበር 2012
ከሞተች ቆይቷል
ሰዓሊና ገጣሚ ገብረ ክርስቶስ ደስታ
ከሞተች ቆይቷል ብዙ ዘመን ሁኑዋል
ብዙ ነበር ጊዜው
ግን ፎቶግራፍዋ፣ ደብዳቤዋም አለ
በጠጉርዋ ጉንጉን የጠቀለለችው
ምን ቀነ ቀጠሮ ነው
ቀን የቀን ጎደሎ
የቀን ጥቁር መጥፎ፡፡
አበባ ሄድኩ ይዤ …
እዚያ አበባ አልጠፋም
በመቃብርዋ ውስጥ አበባ ተኝትዋል፡፡
ስሜቴ ፈነዳ ገላዬን በተነው
ነፍሴን ነቀነቃት
እንባዬ ወረደ ጉንጬን አረጠበው
ለተረሳ ነገር እንዴት ያለቅሳል ሰው!
ለተረሳ ነገር
ምን ጊዜው ቢረዝም . . .
የዚህ አለም ጣጣ እንከራተተኝ
የዚህ አለም ስቃይ እየቦረቦረኝ -
ሲጨንቀኝ ሰውነት
ፍቅሬ ይሁን ያንቺ የኔ መቃብር ቤት፤
ህይወት ነዶ ጠፍቶ ሞት ፍሙን ሲያዳፍን
ያን ጨለማ ጉዋዳ ሄጄ ልተኛበት፡፡
ይመስላል ዘላለም . . .
እሑድ 16 ዲሴምበር 2012
የአክሱም ጫፍ አቁማዳ ~ ደበበ ሰይፉ
ገጣሚ ፣ ጸሐፊ ተውኔትና የሥነጽሑፍ ተመራማሪ ደበበ ሰይፉ
የአክሱም ጫፍ አቁማዳ PDF
/ደበበ ሰይፉ/
ትግራይ ላከ ወሎ ጋ አበድሮኝ ብሎ አንድ ቁና ጤፍ
ወሎም አፈረና የለኝም ማለቱን ባህሉን መዝለፍ
ቆሌውን መንቀፍ
ላከ ወደሸዋ ምናልባት ቢሰጠው ለሰው እሚተርፍ።
ሸዋም አፈረና የለኝም ማለቱን ወደ ሐረር ዞረ
ሐረርም መልሶ ባሌን አተኮረ
ባሌም ወደአርሲ አርሲ ሲዳሞን
ሲዳሞም ተክዞ፣ ግን የለኝም ብልስ ማን ያምነኛል ብሎ
ወደ ጋሞ ላከ አቁማዳ ጠቅሎ።
ጋሞን ብርድ መታው ሐዘን ገባውና
የራሱን ምንዳቤ የግል ስቅየቱን ችሎት በጥሞና
በጋቢ ጀቡኖ የልቡን ጠባሳ ሲኖር እንደ ደህና
ዛሬ የወንድሙን የእርዳኝ አቤቱታ መስማት አልቻለና።
አውጥቶና አውርዶ ላከ ወደ ከፋ እጅግ አስተዛዝኖ
ከሀፍረት ያድነኛል ከረሃብ ያወጣኛል ሲል በአያሌው አምኖ።
ቅዳሜ 8 ዲሴምበር 2012
ረቡዕ 5 ዲሴምበር 2012
NILE: A Poem by Tsegaye Gebre-Medhin

I am the first
Earth Mother of all fertility
I am the Source
I am the Nile I am the African I am the beginning
O Arabia, how
could you so conveniently have forgotten
While your
breath still hangs upon the threads of my springs
O Egypt, you
prodigal daughter born from my first love
I am your Queen
of the endless fresh waters
Who rested my
head upon the arms of Narmer Ka Menes
When we joined
in one our Upper and Lower Lands to create you
bosom of my
being
How could you so
conveniently count down
In miserable
billions of petty cubic yards
The eternal
drops of my life giving Nile to you
Beginning long
before the earth fell from the eye ball of heaven,
O Nile, that
gush out from my breath of life
Upon the throats
of the billions of the Earth's thirsty multitudes,
O World, how
could you so conveniently have forgotten
That I, your first
fountain, I your ever Ethiopia
I your first
life still survive for you?
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)















