ልጥፎችን በመለያ Debebe Seifu በማሳየት ላይ። ሁሉንም ልጥፎች አሳይ
ልጥፎችን በመለያ Debebe Seifu በማሳየት ላይ። ሁሉንም ልጥፎች አሳይ

ሐሙስ 17 ጃንዋሪ 2013

ሐዘንሽ አመመኝ/ ደበበ ሰይፉ















ውል አልነበረንም የፍቅር ቀጠሮ
ቃልም አላኖርንም በወግ ተቀምሮ፤
እኔ አንቺን እንዳላይ
አንቺ እኔን እንዳታይ አምባችን ተቃጽሮ
ዕጣችን ተካሮ፤
ቀለምሽ ከዐይኔ አሻራሽ ከጣቴ ባይጠፋ ተማትሮ
(እትብት እምብርት ሁኖ እንዲኖር ደድሮ)
ይኸው አካሄደን በድንገት ዘንድሮ።
የገጽሽ ብርሃን ቢጠይም ፀዳሉ
ድምፅሽ ቢቀጥንብኝ ቢሠልብኝ ቃሉ
ወዘናሽ ቢማስን ዛሬ ያለውሉ
በእጆችሽ ጨበጠኝ ሐዘንሽ ሥዕሉ
ሐዘንሽ አመመኝ
ብሶትሽ ጠቀሰኝ።

እሑድ 16 ዲሴምበር 2012

የአክሱም ጫፍ አቁማዳ ~ ደበበ ሰይፉ


ገጣሚ ፣ ጸሐፊ ተውኔትና የሥነጽሑፍ ተመራማሪ ደበበ ሰይፉ















የአክሱም ጫፍ አቁማዳ PDF
/ደበበ ሰይፉ/

ትግራይ ላከ ወሎ ጋ አበድሮኝ ብሎ አንድ ቁና ጤፍ
ወሎም አፈረና የለኝም ማለቱን ባህሉን መዝለፍ
            ቆሌውን መንቀፍ
ላከ ወደሸዋ ምናልባት ቢሰጠው ለሰው እሚተርፍ።
ሸዋም አፈረና የለኝም ማለቱን ወደ ሐረር ዞረ
ሐረርም መልሶ ባሌን አተኮረ
ባሌም ወደአርሲ አርሲ ሲዳሞን
ሲዳሞም ተክዞ፣ ግን የለኝም ብልስ ማን ያምነኛል ብሎ
ወደ ጋሞ ላከ አቁማዳ ጠቅሎ።

ጋሞን ብርድ መታው ሐዘን ገባውና
የራሱን ምንዳቤ የግል ስቅየቱን ችሎት በጥሞና
በጋቢ ጀቡኖ የልቡን ጠባሳ ሲኖር እንደ ደህና
ዛሬ የወንድሙን የእርዳኝ አቤቱታ መስማት አልቻለና።
አውጥቶና አውርዶ ላከ ወደ ከፋ እጅግ አስተዛዝኖ
ከሀፍረት ያድነኛል ከረሃብ ያወጣኛል ሲል በአያሌው አምኖ።