አንድ እጅግ ያዘነ ሰው ባር ውስጥ ተቀመጦ ፊት ለፊቱ ያለውን መጠጥ ላይ እንዳተኮረ ሰላሳ ደቂቃ በላይ ቆየ። በዚህ መሐል አንድ ጠጪ ወደርሱ ቀርቦ ጠረጴዛው ላይ ያለውን መጠጥ አንስቶ ሻት አደረገው።
ምስኪኑ ሰው ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ጀመረ። “ተረጋጋ ወንድሜ፣ ለጨዋታ ነው የጣሁብህ። ሌላ መጠጥ አዝልሃለሁ” ሲል ሊያረጋጋው ሞከረ።
“ነገሩ አልገባህም፣ ዛሬ ለእኔ ሲበዛ በመከራ የተሞላ ቀን ነው። ጠዋት መስሪያ ቤት ስብሰባ ላይ ጥቂት ደቂቃ አርፍጄ ብገኝ አለቃዬ ከስራዬ አሰናበተኝ። ወደ ቤት ለመመለስ መኪናዬን ወዳቆምኩባት ቦታ አመራሁ። በቦታው ግን አልነበረችም። መኪናዬ ተሰርቃ ነበር። ለፖሊስ አመለከትኩ። እነሱ ግን ምንም ሊረዱኝ እንደማይችሉ ገልፀው አሰናበቱኝ። በጣም እያዘብኩ በኮንትራት ታክሲ ወደቤት ስመለስ ሞባይሌና የእጅ ቦርሳዬን ረስቼው ወረድኩ። ከዚህ ሁሉ መከራ ልታፅናናኝ የምትችለው ባለቤቴ ብቻ ነበረች። እሷም ቤት ስገባ ከአትክልተኛችን ጋር አልጋ ላይ ተኝተው ደረስኩ። ነገሮች ሁሉ ከአቅሜ በላይ ሆኑ። በመጨረሻ ወደዚህ ባር የመጣሁት ራሴን ላጠፋ ነበር። አንተ ግን መርዜን ጠጣህብኝ።”