ሐሙስ 1 ኖቬምበር 2012
እሑድ 28 ኦክቶበር 2012
"የኢትዮጵያ ግጥም ፈርጥ" ለአጼ ይስሓቅ በዘመኑ ከተገጠመላቸው የተወሰደ
ዓፄ ይስሐቅ
ቀዳማዊ አጼ ይሥሓቅ
በዙፋን ስማቸው "ዳግማዊ ገብረ መስቀል" ሲባሉ እ.ኤ.አ ከ1414-1429 የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የነበሩ ናቸው።
የቀዳማዊ አጼ ዳዊት ሁለተኛ ወንድ ልጅ ሲሆኑ የቀዳማዊ ቴዎድሮስ ታናሽ ወንድም ናቸው።
በግብጽ ቆብጦች ላይ በሚካሄድው ዘመቻ ምክናያት ብዙ ኮብቶች ወደኢትዮጵያ በዚሁ ዘመን ተሰደዱ። ከነዚህ ውስጥ ፋቅር አል-ዳዋ የተሰኘው የግብጹ ማምሉክ ባለሟል ይገኝበታል። ይህ ባለሟል በይስሓቅ ግዛት ውስጥ ተሰሚነት በማግኘቱ የአገሪቱን የግብር ስርዓት በመለወጥ በግብጽ ማምሉኮች በሚሰራበት መልኩ እንዲሆን አድርጓል። የንጉሱንም አለባበስ በመቀየርና መስቀል እንዲይዝ በማድረግ ንጉሱ ከቀሪው ህዝብ ለየተ እንዲል አድርጓል። በኋላም በራሳቸው በግብጽ እስላሞች መካከል በተነሳ ጠብ የቁስክፍለ ሃገር ገዢ የነበርው አሚር አል-ቱንቡጋ አል-ሙፍሪቅ በአጼ ይስሓቅ መንግስት ባለሟልነትን አግኝቶ በኋላ የንጉሱ ሰራዊት እንዲሻሻል አድርጓል። ይህ ግብጻዊ ለኢትዮጵያው ሰራዊት ካስተዋወቃቸው ነገሮች ውስጥ የእሳት ችቦ መወርወሪያ ዘዴንና የሻሞላ ውጊያን ይይዛሉ። እንደ ታሪክ አጥኝው ጅ.ቢ.ኸንቲንግፎርድ አባባል ከሆነ የኢትዮጵይ ነገስታት ቋሚ ዋና ከተማ ማድረግ ያቆሙት በዚሁ ንጉስ ዘመን ነበር።

ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)