ብቻዬን
/ታገል ሰይፉ
-------
ሰዎች
ርቀው ካጠገቤ-
ዙሪያዬን
ከቦኝ ፀጥታ
በፀጥታው
መሐል ስጓዝ-
ናፍቆቴን
ውጬ በዝምታ. . .
ቅጠሎች
ተንሾካሾኩ-
ገባኝ
እኔም ሀሜታቸው
ከብቸኝነት
በርሃ-
ብቻውን
ቀረ ማለታቸው፡፡
ጥላዬም
ይህን ሰማና
በዝምታ
ተከተለኝ
ሁሉም
ቢከዱህ እንኳን
እኔ
አልከዳህም እያለኝ. . .
እባክህ
ተወኝ ጥላዬ
አትሞግተኝ
በሽንገላ
ማየቴ
አይቀርም ከቆየሁ-
አንተም
ስትከዳኝ እንደሌላ…
---------
ታገል
ሰይፉ(የካቲት 3-1986)
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
ብቻውን
/ ወንድዬ አሊ
-------
ብን
. . . እብስ
ብን
. . . እብስ
ከጥላው
ተጣልቶ … ከራስ ተሰራርቆ
ከራስ
ጠረን ሸሽቶ … እስትንፋስን ርቆ
በመብረቋ
ደቆ
ብን
. . . እብስ
ብን
. . . እብስ
ሌት
ቀን . . . ደንብዞ
በ'ጣ
ተክሏ መሮ - ሕመሟን ደንዝዞ
ማመን
. . . መተማመን
ቅዠቷን
. . . ደንግጦ
ቀጋ
ጡቷን . . . መጦ
ብን
. . . እብስ
ብን
. . . እብስ
አለኋችሁ
ላይል … አለሁ ባይም አጥቶ
ጠሪ
ባያገኝም … እሱም ለወይ ታክቶ
በሰው
ጫካ መሐል … ቀልብያው ሸፍቶ
የመሐል
አጠገብ … እሩቅ ተሰውሮ
ባይተዋርነትን
… ሰቀቀኗን ነፍሮ
ነጠላውን
ቀዞ
በቅንዓት
… ነብዞ
ሌላ
ምንም አይደል
ታሽቶ
- መታሸቱ
ብን
. . . እብስ ማለቱ
ብቻው
ብቻ … ሲቀር
ብቻ
ሲቀር አይደል!? … በብቸኝነቱ!
------
ወንድዬ
አሊ፣ ወፌ ቆመች መጽሐፍ