(ኄኖክ ስጦታው)
ባለሶስት ፉርጎ ነው፤ ይጓዛል ባቡሩ፤ ቆየሁ ተሳፍሬ የኋላኛው – ትላንት፣ የፊተኛው – ነገ፣ መሀለኛው – ዛሬ … * የታለፈ ትላንት፣ ያልተኖረ ነገ፣ ሃሣብ ውስጤ ሰርጎ (ወጥሮ ይዞኛል) ፊት ላይሆን—ወይ ኋላ፣ መሐለኛው ፉርጎ።