ረቡዕ 16 ኤፕሪል 2014

የኄኖክ-diary (በፌስቡክ ተከፈተ፡፡)


ውድ የእልፍኜ ታዳሚያን፤ የኄኖክ-diary በፌስቡክ መንደር የከፈትኩት አዲሱ ገጼ ነው፡፡

የኄኖክ-diary
የኄኖክ-diary
ማነው ዳየሪዬን ማንበብ የሚፈልግ?  የኄኖክ-diary ፡-  https://www.facebook.com/henokspad በዚህ ሊንክ ገብተው ላይክ በማድረግ ይከተለኝ፡፡

ሰኞ 14 ኤፕሪል 2014

የበዓል ሰሞን ፍተላዎች - ኄኖክ ስጦታው



በግ ከመግዛት በግ የገዛንባቸውን ዘመናት በማሰብ መፈተል ይቀላል፡፡ 

ፍተላ 1 (እውነተኛ)

ለአዲስ ዓመት ቅበላ ሸመታ በወጣንበት ባንዱ የሆነ ነው፡፡ ሶስት ሆነን ገበያ ወጣን ፡፡ ሁለታችን ሙክት ስንገዛ ሶስተኛው ጓደኛችን ደግሞ እኛ አንድ ሙክት በገዛንበት ሂሳብ ሁለት ትንንሽ በጎችን ሸመተ፡፡ ሊቀልባቸው ነው ሊቀለባቸው?¡? . . . ለምን ሁለት ትንንሽ በጎች እንደገዛ ጠየቅነው፡፡ በኩራት ነገረን፡፡

እቅዱ እንዲህ ነው፤ አንዱን ለዘመን መለወጫ ይባረካል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ለቅዱስ ዮሐንስ፡፡ 

በቃ! የሸመታ ጥበቡ አሪፍ ቅጽል ስም አሰጠው፡፡ቬንገርተባለ፡፡

በሌላ ቀን . . .

ባለ ሁለት በጉን ሰው (“ቬንገር) በአካል የማያውቁ የኔ ጓደኞች ሁሉ ስለሆነው ተረኩላቸው፡፡ አብርሃም ጆሮ ደረሰ፡፡ አብርሃም ዛሬ የነገርከውን ቀልድም ይሁን ቁምነገር ሪሚክስ አድርጎ በሌላ ቀን መልሶ ለራስህ ይነግርሃል፡፡ ማን እንደነገረው ቢረሳም የተነገረውን የማይረሳ ጓደኛ ኖሮህ አያውቅም? እንደዚህ አይት ሰው ነው፡፡ 

ለገና በዓል ዋዜማ አብርሽ አብሮኝ ገበያ ወጣ፡፡ቬንገርምነበር፡፡ የበግ ወሬ ተነሳ፡፡ 

አንዱ የተባለውን ልንገራችሁ . . . ” ብሎ ወሬ ጀመረ፡፡ አብርሽ፡፡አንድ ትልቅ በግ በሚገዛበት ገንዘብ ሁለት ትናንሽ በጎች ገዝቶ ቤቱ ሲገባ ምን እንዳሉት ታውቃላችሁ ??!! . . .”

እኔናቬንገርተፋጠጥን፡፡ አብርሽ ወሬውን ቀጠለ፡፡ እስኪጨርስ ታግሼ እንዲህ አልኩት፡-

እሱ ነውቬንገር፡፡ ተዋወቀው፡፡

አብርሽ ደነገጠ፡፡ ድንጋጤው ደግሞ እኛን አሳቀ፡፡ ከሳቁ በኋላቬንገርወደጆሮዬ ተጠግቶ፡-

በስሜ ካልጠራኸን ጓደኛዬ አይደለህም!” አለ፡፡ እንዳለኝም አደረኩ፡፡ (በተቃራኒው ይህን ወሬ ስጽፍ እውነተኛ ስሙን አልጠራሁም፡፡)

የዛን እለትቬንገርትልቅ በግ ገዛ! አብርሽ ግንቬንገርገዝቷቸው ከነበሩ ትናንሽ በጎች ያነሰች በግ ገዛ፡፡

ቬንገርበተራው - 

በግ ገዛሁ እንዳይል ንገረው፡፡ የበግ ለምድ የለበሰች ዶሮ ገዛሁ ይበል፡፡ 

ፍተላ 2 (በእውነት የሆነ)

እንዲሁ በሌላው በዓል . . . ሁለት ሆነን በግ ሸመትን፡፡ ዶሮ ማነቂያ የምናውቀው አንድ ሌላ ወዳጃችን ድክም ያለች በግ እንደ ቦርሳ አንጠልጥሏት መጣናበፒያሳ የምታልፉ ከሆነ እባካችሁ ሸኙኝአለን፡፡ ተባበርነው፡፡ የእርሱ በግ ከሁለት ቀንዳም በግ መሐል የመኪና ኪስ ውስጥ አስገባንና ጉዞ ተጀመረ፡፡ መንገድ ላይ በመኪና ኪሱ ውስጥ የጦፈ የመንጓጓት ድምጽ ተሰማ፡፡ ያው የተለመደ የበጎች መንፈራገጥ እንደሆነ በማሰብ ፒያሳ ደረስንና መኪናው ቆመ፡፡ ኪሱ ተከፈተ፡፡ መጨረሻ የተጫነችው በግ ነስር በነስር ሆናለች፡፡ 

ጭንቅላቷን ወደሰማይ ቀና አድርገህ ያዝላት!” አልነው፡፡ እንደተባለው አደረገ፡፡ 

የበጓ ባሉካሶፍት ! ሶፍት! እባካችሁን ሶፍት . . .” አለ ብለን አስወራን፡፡ ነገሩ ካለፈ በኋላ፡፡ 

በወቅቱ አቅማችን የፈቀደው የመጀመሪያ ርዳታ ተረብ ነበር፡፡ የህክምና ጉዳይ የማይታሰብ በመሆኑ . . . እንደ ሻንጣ አንጠልጥሎ ወደ ቤቱ ሮጠ፡፡ 

በረንዳ ላይ ታስራ ለመጮህ ያልታደለችው በግ በበአል ዋዜማ ትባረካለች፡፡እንዳለው ሼክስፒር /ለአባባሉ ክብደት ልስጠው ብዬ ነው/ እንዲሁም ሆነ፡፡ 

ፍተላ 3- (በቢሆን የተፈተለ . . . የበዓል ትርርብ ላይ የተፈጠረ)

ቀጭን ድምፅ ያለው ወዳጃችን ፍየል ገዛ፡፡ ፍየሏ ስትጮህ የሰው ስም የምትጠራ ነው የምትመስለው፡፡በቀለ!” የምትል፡፡ ደግሞም እንደዛ ነው የምትለው፡፡ ቤቱ ወስዶ አሰራት፡፡ መጮህ ጀመረች፡፡ በቀጭን ድምጿ፡፡

በቀለ! በቀለ! በቀለ!”

በሩ ተንኳኳ፡፡ ባለ ፍየል ጓደኛችን በሩን ከፈተ፡፡ ጎረቤቱ አቶ በቀለ ከደጅ ቆመው፡-

አቤት ! ጠራኸኝ??”

በቀጭን ድምፁ ኧረ እኔ አልጠራሁዎትምአለ፡፡ እንዳልጠራቸው በመኃላ አረጋገጠ፡፡

እንዲህ እያሉ ሄዱ፣የማርያም ብቅል እየፈጨሁ ነው!” 

እሱ በተራው አፀፋ ተረብ ሰነዘረ፡፡

ኄኖክ ከጩኸት ይልቅ ፉጨት የሚቀናት ዶሮ ገዛ፡፡ ሊያርዳት ሲልቆቆቆቆቆይ . . . “ቆቆቆቆቆይ . . .!” ስትል የሰሙ እናቱ ለዶሮዋ አዝነው አልያም ዶሮዋ እያጣጣረች እንደሆነ ተረድተው፡-

ምነው ኄኖክ! ቆይ እያለችህ ልታርዳት!?! ”

እና ምን ላድርጋት??”

ትንሽ ከታገስክ መሞቷ ስለማይቀር ያኔ ትቀብራታለህ፡፡