(ኄኖክ ስጦታው ናኁሰናይ)
“ነበር” ላይ ሊያበቃ፣ የ“ነው” ባይ አቅጣጫ፤
ከ"ነው" እና "ነበር"፣ የታል የኔ ምርጫ?
•
መድረሻው መነሻ
መነሻው መድረሻ
ጠይቅ “የታል” ብለህ… “የታል ውጣ—ውረድ”?
(ሕይወት መሰላል ነው፤ የእርብራብ መንገድ!)
•
የጥያቄ ምላሽ፣ በምጥ ላይወለድ
“እውነት” ካስጨነቀህ፣
በስንዝር ቦታ ላይ፣ ጋት ጨምር… ተራመድ
መልሱን ተወውና፣ መጠየቅን ውደድ
ውጣ
ወይም
ውረድ!