(ኄኖክ ስጦታው)
በእንክርዳድ ማሳ ጥቂት ስንዴ በቅሎ ይስፋፋ ጀመረ “እሕል ነው” ተብሎ። * ስንዴ ለሆድ ሲባል፣ በሰው መኮትኮቱ ተነቅሎ ቢጣልም፣ እንክርዳድ ነው ብርቱ ሳይዘሩት ይበቅላል፣ የት ይሂድ ከርስቱ?! *
ኮትኩቶ ማሳደግ፣ ቀልቦ ማደለብ፣ የሰው ታላቅ ዘዴ “ ደረሰ… በሰለ…” የሚሉኝ በዙሳ ፣ ሊበሉኝ ነው እንዴ?!