እንዳይነግርህ
አንዳች እውነት ! - ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን
ደንስ ጎበዝ ! ደንስ
ጀግና
ክራቫትህን አውልቅና
ሃሳብህን ልቀቀውና
ኮትክን ሸሚዝክን ጣልና
ርገጥ ፣ ጨፍር ፣ ደንስ
ጀግና !
ያን የሙዚቃህን ናዳ
፣ የኮንትራባሱን መብረቅ
ልቀቀውና ይድብለቅለቅ
ምድር በሆይታ ይጥለቅለቅ
!
ምንም-ምንም እንዳታስብ
፣ ሁሉን-ሁሉን እንድትረሳ
ደንስ ! ካካታው ይነሳ
ጨፍር ፣ ወለሉ እስኪበሳ
....
ሃይ-ሃይ ! ዋይ !
ሃይ-ሃይ ! በልበት
የጃዝ ፋንፋር አንኳኳበት
ራስክን እንዳታስብበት
፤
ሆ ! በል እሪ ! በል
ምታበት
ፎክርበት ፣ አቅራራበት
አናፋበት ፣ ሸልልበት
የሲቃ ሳቅ አስካካበት
ሆያ-ሆዬ ! በል ጩኽበት
ኡኡታህ መንኮራኩርክን
፣ እስኪያሰጥመው አጓራበት
ጭንቅላትክን ግዘፍበት
፣ ውቀጥበት ፣ ውገርበት ፣ ....
ዝግ ብሎማ ያሰበ እንደሁ
፣ ይነግርሃል አንዳች እውነት !
-----------
ባለቅኔ
ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን