እሑድ 28 ኦክቶበር 2012

"የኢትዮጵያ ግጥም ፈርጥ" ለአጼ ይስሓቅ በዘመኑ ከተገጠመላቸው የተወሰደ


ዓፄ ይስሐቅ




ቀዳማዊ አጼ ይሥሓቅ በዙፋን ስማቸው "ዳግማዊ ገብረ መስቀል" ሲባሉ እ.ኤ.አ ከ1414-1429 የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የነበሩ ናቸው። የቀዳማዊ አጼ ዳዊት ሁለተኛ ወንድ ልጅ ሲሆኑ የቀዳማዊ ቴዎድሮስ ታናሽ ወንድም ናቸው።

በግብጽ ቆብጦች ላይ በሚካሄድው ዘመቻ ምክናያት ብዙ ኮብቶች ወደኢትዮጵያ በዚሁ ዘመን ተሰደዱ። ከነዚህ ውስጥ ፋቅር አል-ዳዋ የተሰኘው የግብጹ ማምሉክ ባለሟል ይገኝበታል። ይህ ባለሟል በይስሓቅ ግዛት ውስጥ ተሰሚነት በማግኘቱ የአገሪቱን የግብር ስርዓት በመለወጥ በግብጽ ማምሉኮች በሚሰራበት መልኩ እንዲሆን አድርጓል። የንጉሱንም አለባበስ በመቀየርና መስቀል እንዲይዝ በማድረግ ንጉሱ ከቀሪው ህዝብ ለየተ እንዲል አድርጓል። በኋላም በራሳቸው በግብጽ እስላሞች መካከል በተነሳ ጠብ የቁስክፍለ ሃገር ገዢ የነበርው አሚር አል-ቱንቡጋ አል-ሙፍሪቅ በአጼ ይስሓቅ መንግስት ባለሟልነትን አግኝቶ በኋላ የንጉሱ ሰራዊት እንዲሻሻል አድርጓል። ይህ ግብጻዊ ለኢትዮጵያው ሰራዊት ካስተዋወቃቸው ነገሮች ውስጥ የእሳት ችቦ መወርወሪያ ዘዴንና የሻሞላ ውጊያን ይይዛሉ። እንደ ታሪክ አጥኝው ጅ.ቢ.ኸንቲንግፎርድ አባባል ከሆነ የኢትዮጵይ ነገስታት ቋሚ ዋና ከተማ ማድረግ ያቆሙት በዚሁ ንጉስ ዘመን ነበር።



ከአክሱም ነገሥታት በኋላ የመጀመሪያውን ከአውሮጳውያን መሪወች ጋር ግንኙነት ያደረገው ይሄው ንጉስ ነበር። ለምሳሌ ለአራጎን መሪ ለነበርው አልፎንሶ አምስተኛ በ1428 ዓ.ም. በእስላሞች ላይ የተባበረ ሃይልን ለመመስረት ደብዳቤ ልኳል። በዚሁ ደብዳቤ የጋብቻን ነገር ያወሳ ሲሆን ህጻኑ ዶን ፔድሮ ከእጅ ጥበብ አዋቂወች ጋር ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የይስሓቅን ሴት ልጅ እንዲያገባ ያትታል። አልፎንሶ ለይስሓቅ የመለሰለት ደብዳቤ ባይገኝም ለይስሓቅ ተከታይ ለአጼ ዘርዓ ያዕቆብ /በዘውድ ስማቸው ቆስጠንጥንዮስ ከአባታቸው ቀዳማዊ ዳዊት እና ከእናታቸው ንግስትክብረ እግዚ በ1399 እ.ኤ.አ. ከአዋሽ ወንዝ አጠቀብ ትገኝ በነበረው ትልቅ ተብላ በምትጠራው መንደር የድሮው ፈተገር ክፍለ ሐገር ተወለዱ። የነገሡበትም ዘመን 1434 - 1468 እ.ኤ.አ. ነበር። ያረፉትም በደጋ ደሴት፣ ጣና ሃይቅ ነው / በ1450 በደረሰ ደብዳቤ ደህንነታቸው እስከተጥበቀ ድረስ እጅ ጥበበኞችን በደስታ ወደኢትዮጵያ እንደሚልክና ከአሁን በፊት የላካቸው 13 ጥበበኞቹ በመንገድ ላይ እንደጠፉ ሳይጠቅስ አላለፈም።


በኒሁ ንጉስ ዘመን በፈላሾች በተነሳ አመጽ ምክንያት ንጉሱ ወደወገራ ዘምተው አመጸኞቹን ኮሶጌ ላይ በማሸነፍ አመጹን አረገቡ። በዚያውም ደብረ ይሥሓቅ የተሰኘውን ቤተክርስቲያን ለድሉ ማስታወሻ ኮሶጌ ላይ አሰሩ። . ንጉሱ ተመልሰው ከአገው ምድር ባሻገር ያለውን የሻንቅላ ምድር ላይ ዘመቻ አካሂደዋል። በደቡብ ምስራቅ ደግሞ ከአረብ አገር የተመለሱትን የሳድ አዲን ፪ኛ ልጆች ወግተዋል።


በዚሁ ዘመን የተጻፈ፣ በታሪክ አጥኝው ኢኔርኮ ቼሩሊ "የኢትዮጵያ ግጥም ፈርጥ" የተባለ አጼ ይስሓቅን የሚያወድስ ግጥም እስካሁን ይገኛል። በፒ.ዲ.ፍ መልኩ ተዘጋጅቶ ቀርቧል።

ታሪክ አጥኝው ታደሰ ታምራት ይስሓቅ ከሙስሊሞች ጋር ሲዋጋ ወደቀ ይበል እንጂ ዋሊስ በድጅ በርግጥም በወንጀል እንደተገደለና በተድባባ ማርያም እንደተቀበረ ይናገራል።

ለአጼ ይስሓቅ በዘመኑ ከተገጠመላቸው የተወሰደ


ዣን ይስሐቄ ትኩር
ትኩረቱም ተምክር
የዣን ይስሐቄ ነገር
ብሐብል በቃል ጎጃም ንግር
ሓፍሶ አይፈጁ አፈር
መትሮ አይፈጁ ግራር
እስኩ ይንገር
የአሳታዊ ዱር
እንዴት ያስደነግጽ
ገጽኹ የዣን ይስሐቄ እንዴት ያስደነግጽ
ዣን ይስሓቄ ገጽ
ፈረስ ሰሮ ሲጋየጽ
ሠላቲን ኂዞ የግብጽ
ዛቢያው ያይታውቅ ዕጽ
ማን ይሓይኽ ገጽ በገጽ
ወምበዴ ጠፋ ለድምጽ
ዓይን በፍልሕ ስታፈርጽ
እጅ በብልሕ ስትቆርጽ
ጥበብሕ የግብጽ
ኃይልሕ የሕንጽ እንዴት ታስደነግፅ
ደንጊያ በቁልቁለት ስሮጽ
እርሱ በእርሱ ሲፋለጽ
እንዴት ያስደነግጽ፣ እንዴት ታስደነግፅ
ኮከብ ትመስል ዣን በጽሩ ሰማይ ሲሮጽ
ወደ ምዕራብ ሲሠርፅ
ገጽኹ እንዴት ያስደነግፅ
ሲሬ ሠራዌ የመስል ዣን
ሐምበል አልብሶ ረመጽ
ጎድን በሪም ሲፈጸፍጽ
ሐንገት በሰይፍ ሲቆርጽ
ገጽኹ እንዴት ያስደነግፅ
ዣን ይስሐቄ ገጽ
ምላት የመስል ዣን
ሳፍ ለሳፍ ካንፈርዓጽ
ወርካ ከስሩ ነቅሎ ሲያሮጽ።
እንዴት ያስደነግፅ
ገጽኹ የዣን ይስሐቄ እንዴት ያስደነግጽ
ዣን ይስሐቄ ገጽ። ዣን በድል እሳት
ጽርሓ ንግስት ታቦት
እንደ ተኮስዋት በእሳት
ፈረስሕን ናቀብል
በቅሎኽን ናቀብል
አንጥፋ ለዘር
አንበሳ ዳዊት ትኳር
በደበናኽ መገን
በፈረስኽ መገን
በሪምኽ መገን
በምሽትኽ መገን
በሕጻናትህ መገን
አማስለሕ አትፍጀን
እኛስ ፈቃደኛነን
እንስጥ መንግስትኽን
ፈረስ የተፈተን
ወርቅ የተመዘን
ሓበጥ ቂራጥ ብለን
ናድርስ መንግስትኽን
አማስለኽ አትፍጀን . . .


1 አስተያየት: