ሰኞ 27 ሜይ 2013

የትም የተፈጨ ዱቄት አንበላም - ታሪካዊ ደብዳቤ - በፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም


.....“የትም ፍጭው፣ ዱቄቱን አምጭው” የሚሉ አይጠፉም፡፡ ግን ዱቄቱ የሚፈጭበት መጅና ወፍጮ ንፅህና፣ የሚፈጭበት ቤት ነዋሪዎች ጤንነት፣ ..... የእንጀራውን ጣእምና ተበይነት ይወስነዋል፡፡ ህይወት የትም የተፈጨ ዱቄት የሚበላበት ዘመን አይደለም፡፡ ያልፈጩትን እህል ከውርደት ጋር በልቶ ከመኖር በረሃብ መሞት ይሻላል፡፡ በኩራት ኖሮ፣ በኩራት ካልተሞተ ህይወት ሌላ ምን ትርጉም አለው?

በ1995 አእ የስዊስ መንግስት 10ሺ ዶላር ለኢሰመጉ ከሰጠ በኋላ፣ በገንዘቡ ዋጋ ኢሰመጉን መግዛት የሚችል መስሎት፣ “ኢሰመጉ ባወጣው ዘገባ መንግስትን ያለአግባቡ ነቅፏል” በማለት ኢሰመጉን አወገዘ፡፡ በጊዜው የኢሰመጉ ሊቀመንበር የነበሩት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም የሚከተለውን ደብዳቤ ለስዊሱ አምባሳደር ጻፉለት፡፡ ደብዳቤው የተጻፈው በእንግሊዘኛ ነበር፡፡ ግን የተጠቀሰውን የሼሊን ውብ ግጥም በአማርኛ ማንበብ ስለፈለግሁ ደብዳቤውን በሙሉ ወደ አማርኛ ተርጉሜዋለሁ፣ ለሚገኘው የትርጉም ስህተት አስቀድሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡

ይህ ታሪካዊ ደብዳቤ፣ ኢትዮጵያውያን የትም የተፈጨ ዱቄት እንደማንበላ በግልፅ የሚያሳይ ነውና ህፃናትም በቃላቸው ሊያጠኑት ይገባል፡፡

ኦክቶበር 9. 1995
ለክቡር ዶክተር ፒተር አ.ሽዋይዘር
የስዊዘርላንድ አምባሳደር
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ክቡር ሆይ
ምናልባት፣ (ደብዳቤዬን) በሼሊ “የፍቅር ሽሽት” መጀመሩ ተገቢ ሳይሆን አይቀርም፡፡
ፋኖሱ ሲተረከክ
          የአቧራ ላይ ብርሃን ያከትማል
ደመናው ሲበተን
          የቀስተ ደመናው ግርማ ይነጥፋል
ዋሽንቱ ሲሰበር
          ጣፋጭ ድምፆች ይተናሉ
ከንፈሮች ተናግረው ሲያበቁም
          የፍቅር ቃናዎች ይረሳሉ፡፡

ከአምባሰደሮች ሁሉ የላቁ የኢሰመጉ ወዳጅ እንደነበሩ አለመርሳታችንን (በቅድሚያ) ላረጋግጥልዎ እወዳለሁ፡፡ ቀደም ሲል የሞራል ድጋፍ እንዳደረጉልንም አልረሳንም፡፡ ለዚያም ውለታው አለብን፡፡

ከኢሰመጉ ጋር ያለዎት የቅርብ ግንኙነት ሳይሆን አይቀርም የትስስሩ ጥንካሬ በዚህ አጋጣሚ ለፈተና የተጋለጠው፡፡ ትስስሩም ደካማ መሆኑ በግልጽ ታወቀ፤ እንዲያም ሆኖ የመታውን ማእበል መቋቋም ተሳነው፡፡ ለመርህ የነበረንን አክብሮት ትተን በነበረን የጋራ ስሜት ምን ያህል መልካም እንደሠራን መገንዘቡ ከኛ ይልቅ ለክቡርነትዎ ግልፅ ነው፡፡ ክቡርነትዎ 10000 ዶላር የሚገመት ሃብት የማባከን ስሜት እንደተጫጫነዎ ያስታውቃል፡፡ ለዚህም የብክነት ስሜትዎ ማካካሻ ብሄራዊ ራታችንን፣ ሰብአዊ ክብራችንን እና ለመርህ ያለንን ተገዥነት እንድንሸጥልዎ ያደረጉት ሙከራ ምን ያህል እንዳስቆጣን ክቡርነትዎ ሊገነዘበው ይገባል፡፡ እንደ ሸክስፒር አባባል፣ ጣፋጭ ነገሮች በምግባራቸው ወደ ኮምጣጣነት ይቀየራሉ፡፡

በመንፈስ ደሃ እንዳልሆንን ክቡርነትዎ አይጠራጠሩም፡፡ ገንዘብዎን ለመመለስ ረዥም ጊዜ ስለወሰደብንም ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ውግዘት ከኢሰመጉ የባንክ መዝገብ ህገወጥ እገዳ ጋር ተጣምሮ መምጣቱን ክቡርነትዎ ያውቀዋልና፡፡ ሆኖም፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ከኢሰመጉ ጎን በመሰለፍ ገንዘቡን በሙሉ እንድከፍል ስላስቻለን ደስ ብሎናል፡፡ ቼኩን ከዚህ ደብዳቤ ጋር አያይዘን ልከናል፡፡

ከመልካም ምኞት ጋር
አክባሪዎ
መስፍን ወልደ ማርያም
የኢሰመጉ ሊቀመንበር

--------

አምሃ አስፋው በገብረክርስቶስ ደስታ ግጥሞች (መንገድ ስጡኝ ሰፊ) ላይ ካቀረቡት ዳሰሳ ላይ ከ”አንድምታ መጽሔት”  የተቀነጨበ /1999ዓ.ም/

5 አስተያየቶች:

  1. what an impressive letter from well-known public figure and elite!!! prof tnx for ur invaluable help in making us a genuine Ethiopian.... and tnk u Heni for ur share of his great thoughts.

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  2. prof, u r quite immpressive

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  3. truth triumphs and all of us should stand for truth and justice not for short term advantage.

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  4. The day will come soon, when people will really know who you are, Professor. Your Napoleon Complex syndrome is more historic, than this letter.

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  5. ፕሮፌሰር መስፍንን ታሪክ አይረሳቸውም። በአጼ ኃይለ ሥላሴ፣ በደርግና ዛሬም አገርና ሰብዓዊ መብትን በተመለከተ አቋማቸው ያልተለወጠ፣ ቢመችም ባይመችም ዝንፍ ያላሉ፣ ወጣቱና አዛውንቱን ማነጋገር የቻሉ፣ በትምህርት ቤትና ባደባባይ ከማስተማር ያልተቆጠቡ ብሎ ታሪክ ያስታውሳቸዋል። እርሳቸው የጻፏቸውን ያህል አነጋጋሪና ትምህርት ሰጭ መጻሕፍት የጻፉ ምሑራን ወዴት አሉ? እድሜና ብርታት ይስጥልኝ። አምሃም እግዜር ይስጥልኝ። ድምጽ አጥፍተህ ብዙ ቁም ነገር እየሠራህ ያለህ ሌላኛው ደግሞ አንተ ነህ።

    ምላሽ ይስጡሰርዝ