2013 ሜይ 28, ማክሰኞ

ትዝታ ዘግንቦት - ኄኖክ ስጦታው




ታሪኩ የዛሬ 22 ዓመት በፊት የተፈጠረ ነው፡፡ 

      እንኳን የተኛን የሞተን የሚቀሰቅስ ከባድ ፍንዳታ ከተኛሁበት ተደራራቢ አልጋ ላይ አስበርግጎ አስነሳኝ፡፡ “ተነሱ! ተነሱ! ”  . . .  ጩኸት ብቻ ነው የሚሰማኝ፡፡ የሚታየኝ ነገር የለም፡፡ ጨለማ ነው፡፡ መብራት ጠፍቷል፡፡ የተደራራቢውን አልጋ መሰላል በዳበሳ አግኝቼ ወረድኩ፡፡ 

      ልብስ እንዴት እንደለበስኩ አላስታውሰውም፡፡ አባቴ እጄን ይዞ ወደውጪ እንደወጣ ትዝ ይለኛል፡፡ ጫማ አላደረኩም፡፡ ባዶ እግሬን አባቴ ወደሚመራኝ መንገድ እሮጥኩ፡፡ አብሪ ጥይት እንደሆኑ የምገምታቸው የእሳት አረሮች በጠቆረው ሰማይ ላይ ይደንሳሉ፡፡ ድንገት እየትጎተለተለ የሚወጣ እሳት ወደ ሰማይ ወጥቶ ወደኛ የሚወርድ ይመስላል፡፡ በአባዬ እጄ መያዙን አልወደድኩትም፡፡ እጄን ከእጁ መንጭቄው እሮጥኩ፡፡ /ትዝታዬን ላሳጥረውና/ ከያኔ ጀምሮ ታዲያ እስካኩንም እየሮጥኩ ነው፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ