poem in pdf እግር እንይ!(ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን)አርቀን ማስተዋል ማለት፣ የኛን ሥልጣኔ ድልድይእግር ማየት ነው ብለዋል፣ እስቲ እንግዲህ እግር እንይ!ያባቶችህ ያይን ድንበር፣ ከተረከዘ ሎሚ ሳያልፍአንተ ግን ጆቢራው-ዘራፍጠፍር አይወስንህ ጉብልጥሎ በዘመንህ ዕድልዓይንህ ባት አልፎ እንዲዋልል፤ቴህ ወዲያ ጀግንነት የለ፣ ተዚህ የከረረ ግዳጅባደባባይ የዱር ገደል፣ ስትናደፍ የእግር አዋጅሌሊቱን በየሌት- ‘ግለብ’፣ ቀኑን ጭምር በጠራራ
ሲነጋ እንደጧት ጆቢራበከተማህ ስታቅራራበዕድሜህ መንከራተት ሥራ፣ካንዱ ቢሮ ሌላው ቢሮ፣ አቦል በረካውን ብለህያገሩን ወሬ ተንትነህተጨቃጭቀህ ተለፋልፈህአመሳጥረህ አቆላልፈህ፣ የዚያን ጉዳይ ከዚህ ጉዳይዘጋግነህ በቡና ምገህ፣ አምተህ ደክመህ ስትለያይ፣በዚህ ብቻ ሳታስቀረው፣ ደሞ አዲሱን የአገር ጠባይከልማድ የቡና ሱስ ጋር፣ የዘመኑን ሳትለያይእስቲ ደሞ አራዳ ወጥተህ፣ በከተማው አደባባይያንዷን ካንዷ ዳሌና ባት፣ እግሯን ከእግር ጋር አስተያይ!ደርቶልህ ያገር ልጅ ቅልጥምዳሌው ባቷ እስኪፈረጥምእየናረ እስኪያስገመግምአንተ አድፍጠህ ከኋላዋ፣ በዓይንህ ሣግ ስታነፈንፍያቺን ልክፍ ያቺን ንድፍእያረክ ስታሾልቅ፣ አንዷ ፈርታ አንዷ ስታፈጥተጠግታህ ባቷ ሲያገምጥ“ዘራፍ” ቀርቶ ቀልብህም “ውይ!”እያለ ወኔህ እግር ይይ!“በሠየጠኑትማ ዘንድአንዱም የባላንጣ ዘዴ፣ የባዕዳን ሥውር መንገድዘመናጥ ጦር መሣሪያ ነው፣ ታዳጊ አገር ለማንጋደድእምነቱን ለማወናበድያንድን ትውልድ የሕልም አቅጣጫወደፊት ሳይሆን ወደታች፣ አመንምኖ ማቀጨጫ!”ቢልህ ፈጥጦ በግልምጫለኅሊናው ማጋለጫናቀው እርግፍ አርገህ ተወው፣ ቴህ ቢጤው ጋር አትንጫጫ፡፡ሠልጥነን ንቀን አልፈነው፣ የይሉኝታን መቀመጫየኛ ዓይን የእግር ነው እንጂ፣ በቅቶት ኅሊና መግለጫ፡፡እርቀን ማስተዋል ማለት፣ የኛን ሥልጣኔ ድልድይእግር ማየት ነው ብለናል፣ አሜን በቃን እግር እንይ!(ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን)‘ለእግረተኞች’ - (፲፱፻፷፫ - ‘ፒያሳ’)እሳት ወይ አበባ
ሐሙስ 10 ጃንዋሪ 2013
እግር እንይ! (ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን)
Labels:
ፈርጦቹ,
free ebook,
poem,
poetry book,
Tsegaye G/Medhin
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
አስተያየቶች ለጥፍ (Atom)
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ