ሰኞ 17 ጁን 2013

ማነው…. ‘ምንትስ’? ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን


ማነው…. ‘ምንትስ’?
ያው መቸም እኔም እንደሰው
አንዳንዴ÷ አንዳንዴ ብቻ÷ ሕሊናዬን እውነት ሲያምረው
ሰብሰብ ብዬ እማስበው
ቀድሞስ ቢሆን ለኔ ብጤ÷ ለኔ ብጤ የሔዋን ዘር
አዳሜ በኔ ላይ በቀር÷ ለኔ መስክሮ አይናገር”
ብዬ ከልቤ ስማከር
እኔው ከኔው ስከራከር
ተጨብጨ እማብላላው
ያው መቸም እኔም እንደሰው
የሐቅ ራብ ነፍሴን ሲያከው
ልቤ ልቤን ሲሞግተው….
እውነትስ ምንትስ ማነው?”
እያለ ነው፡፡ …..

ቅዳሜ 15 ጁን 2013

ቆቅ እና “ማሽሟቀቅ” . . . ከሰማሁት ያስታወስኩትን ያህል - - ኄኖክ ስጦታው



በ1993 መጨረሻ ይመስለኛል፡፡ በሩሲያ ሳይንስና ባህል ማዕከል ገጣሚና ጋዜጠኛ ነቢይ መኮንን የትምህርት ቤት ትዝታውን አንስቶ ተሞክሮውን ያካፈለበት ላይ ሲናገረው የሰማሁት ነው፡፡ አማርኛ አስተማሪያቸው “ቆቅ” በሚል ርዕስ ሁለት መስመር ግጥም እንዲጽፉ አዘው ነው ነገርየው፡፡ ከተማሪዎቹ መካከል አንዱ አማርኛ ቋንቋ ሁለተኛ ቋንቋ ኖሮ የጻፈው ግጥም ለመምህሩ ሊገባቸው አልቻለም፡፡

 እዚያ ማዶ አነዲት ቆቅ
አየኋትኝ ስታሽሟቅቅ፡፡

ተማሪውን አስነስተው “ማሽሟቀቅ” ምን ማለት እንደሆነ ይጠይቁታል፡፡ መልሱን ሰምተው ማርክ ሊሰጡ መሰለኝ፡፡ ተማሪውም እንዲህ ብሎ መለሰ፡-

“እኔ ለራሴ አማርኛ ለማወቅ እያሽሟቀቅኩ ነው”

ታዲያ የቃሉን ፍቺ በቅርቡ (ቅርቡ ጊዜ ያኔ ነው) እንደተረዳው ነቢይ መኮንን ለዛ ባለው አንደበቱ ተናግሮ ነበር፡-
“ገዢው ፓርቲ እያሽሟቀቀብን እንደነበረ የገባኝ አሁን ነው” ብሎ ታዳሚውን አስፈግጓል፡፡(በነገራችን ላይ ይህች የቆቅ “ግጥም” ከግዜያት በኋላ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ “የነገር ጥግ” አምድ ስር  ማንበቤን አስታውሳለሁ)


ነቢይ መኮንን ለታዳሚዎቹ አንድ የግጥም ርዕስ ሰጠ፡፡ “ትዝታ” በሚል ሁለት ስንኝ ግጥም ጻፉ ፤ አለ፡፡ በብርሃን ፍጥነት አንድ ሰው ጽፎ ሰጠው፡፡ አነበበልን፡-

ትዝታሽ ዘወትር ወደኔ እየመጣ
ስለሚያስቸግረኝ ፖሊስ እጠራለሁ፡፡

(አንታራም ግጥም ይሉሀል እንዲህ ነው፡፡)

ሰኞ 10 ጁን 2013

“ነወር”፣ “ነውረኛ”፣ “ነዋሪ” - ኄኖክ ስጦታው

“ነወር”
“ነውረኛ”
“ነዋሪ” 
-
-
-
-

“ነወረ” ማለት . . . “አነወረ፣ አስነወረ፣ አሳፈረ፣ ነውረኛን አደረገ፣ ወይም ተነወረ፣ በነውር ነገር ተከሰሰ” ይለዋል ከሳቴ ብርሃን የአማርኛ መዝገበ ቃላት ፤ በተሰማ ሀብተ ሚካኤል ግጽው የተዘጋጀው፡፡ 

“ነውረኛን” ማለትን ሲፈታው ደግሞ፡- “ነውርን የተመላ፣ ነውርን ከመስራት የማያርፍ(ተነወረ፣ ነውረኛ ሆነ) ” 

“ነዋሪ” ማነው? ካላችሁ . . መልሱ. . . አንድም በመንግስቱ ኅልፈት ጥፋት የሌለበት፣ ሳይለዋወጥ ፣ ጊዜ ሳይወስነው የሚኖር አምላክ ነው፡፡ ሌላም፣ በሕይወት ሥጋ የሚኖር፣ ከቦታው የማይላወስ…. ባለበት ጠንቶ የሚኖር ነው፡፡ ስለዚህም ነው መሰል፣ “ነወር” ስንባል ፣ በተለምዶ “በእግዜር” እንላለን፡፡ 

አሁን አሁን እየተስተዋሉ ያሉት እውነታዎች ስንገመግም አንድ ትልቅ ቁም ነገር ትርጉም አልባ እየሆነ ለመሆኑ ማስረጃ መጥቀስ የማያሻው ጉዳይ ነው፡፡ በማሕበረሰቡ ድንጋጌ (ይህ ድንጋጌ በነዋሪዎች ቅቡልነት /ተለምዷዊ ስምምነት/ አቋም የያዘ ነጥብ ፤ በአብላጫው ተቀባይነት ድምፅ የፀደቀ፡፡) ? 

“ነወር” የሚለውን ቃል ስንበረብረው “ኖር” ከሚለው ቃል በተጨማሪ “ነውር” የሚል ተጻራሪ ፍቺ አቅፏል፡፡ /እንግዲህ እኔ እንደተረዳሁት ነው ትንታኔው/ . . . አንድም ለክብር አንድም ለተግሳጽ የምንጠቀምበት ይህ ባህል ከመጥፋት እንታደገው!

ኄኖክ ስጦታው

ዓርብ 7 ጁን 2013

እግር ኳስና ልጅነት



የኳስ ፍቅር አጠርነቴን የተረዳው ጓዴ ባንድ ወቅት እንዲህ ብሎኝ ነበር፡-
ልጅ ሳለህ አንግል ነበርክ እንዴ?”

አዎ! ልጅ ሳለን እንደዛሬው የመጫወቻ ሜዳ በሊዝ ሳይቸበቸብ በፊት፣ እንደዛሬው ኪስ ቦታዎች ለእነ እንቶኔ በማህበር ሳይመሩበት በፊት፣ የላስቲክ እና የካልሲ ኳስ ብርቅ በነበረበት የልጅነት እድሜያችን፣ እኛ ታናናሾች ለታላቆቻችን የእግር ኳስ ጨዋታ የግብ አንግል እንሆን ነበር፡፡ አሁን ሳስበውካፖርተኒ” /የቆዳ ኳስ/ በሽ ሆኖ፣ እንኳን ሊጫወቱበት አንግል ለመሆን ያልታደሉ የእድሜ ታናሾቻችን እድል አሳዘነኝ፡፡

ኄኖክ ስጦታው- henoksitotaw.blogspot.com

ሐሙስ 30 ሜይ 2013

እንዲህ ቢሆንስ?!

½¬ú: GYz¬b¿ ?Á ''wFXY>¬ú ½wKP HT}… Îo¿¬ú ¬úYÕ FÐpz#¬ú« ÃTW«oz@$ Îúľ« oDÐ ›½w»zw@Œ¬ú Y><Œ HTz…«« Wüαú ÁÓ«`a'' ½Gû>« HŒ¬ú ÓîX ? FÓÔx« ›ÐTð ™ÆTΫ ›«w¬¬ú ŒoT$

ማክሰኞ 28 ሜይ 2013

ትዝታ ዘግንቦት - ኄኖክ ስጦታው




ታሪኩ የዛሬ 22 ዓመት በፊት የተፈጠረ ነው፡፡ 

      እንኳን የተኛን የሞተን የሚቀሰቅስ ከባድ ፍንዳታ ከተኛሁበት ተደራራቢ አልጋ ላይ አስበርግጎ አስነሳኝ፡፡ “ተነሱ! ተነሱ! ”  . . .  ጩኸት ብቻ ነው የሚሰማኝ፡፡ የሚታየኝ ነገር የለም፡፡ ጨለማ ነው፡፡ መብራት ጠፍቷል፡፡ የተደራራቢውን አልጋ መሰላል በዳበሳ አግኝቼ ወረድኩ፡፡ 

      ልብስ እንዴት እንደለበስኩ አላስታውሰውም፡፡ አባቴ እጄን ይዞ ወደውጪ እንደወጣ ትዝ ይለኛል፡፡ ጫማ አላደረኩም፡፡ ባዶ እግሬን አባቴ ወደሚመራኝ መንገድ እሮጥኩ፡፡ አብሪ ጥይት እንደሆኑ የምገምታቸው የእሳት አረሮች በጠቆረው ሰማይ ላይ ይደንሳሉ፡፡ ድንገት እየትጎተለተለ የሚወጣ እሳት ወደ ሰማይ ወጥቶ ወደኛ የሚወርድ ይመስላል፡፡ በአባዬ እጄ መያዙን አልወደድኩትም፡፡ እጄን ከእጁ መንጭቄው እሮጥኩ፡፡ /ትዝታዬን ላሳጥረውና/ ከያኔ ጀምሮ ታዲያ እስካኩንም እየሮጥኩ ነው፡፡

ሰኞ 27 ሜይ 2013

የትም የተፈጨ ዱቄት አንበላም - ታሪካዊ ደብዳቤ - በፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም


.....“የትም ፍጭው፣ ዱቄቱን አምጭው” የሚሉ አይጠፉም፡፡ ግን ዱቄቱ የሚፈጭበት መጅና ወፍጮ ንፅህና፣ የሚፈጭበት ቤት ነዋሪዎች ጤንነት፣ ..... የእንጀራውን ጣእምና ተበይነት ይወስነዋል፡፡ ህይወት የትም የተፈጨ ዱቄት የሚበላበት ዘመን አይደለም፡፡ ያልፈጩትን እህል ከውርደት ጋር በልቶ ከመኖር በረሃብ መሞት ይሻላል፡፡ በኩራት ኖሮ፣ በኩራት ካልተሞተ ህይወት ሌላ ምን ትርጉም አለው?

በ1995 አእ የስዊስ መንግስት 10ሺ ዶላር ለኢሰመጉ ከሰጠ በኋላ፣ በገንዘቡ ዋጋ ኢሰመጉን መግዛት የሚችል መስሎት፣ “ኢሰመጉ ባወጣው ዘገባ መንግስትን ያለአግባቡ ነቅፏል” በማለት ኢሰመጉን አወገዘ፡፡ በጊዜው የኢሰመጉ ሊቀመንበር የነበሩት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም የሚከተለውን ደብዳቤ ለስዊሱ አምባሳደር ጻፉለት፡፡ ደብዳቤው የተጻፈው በእንግሊዘኛ ነበር፡፡ ግን የተጠቀሰውን የሼሊን ውብ ግጥም በአማርኛ ማንበብ ስለፈለግሁ ደብዳቤውን በሙሉ ወደ አማርኛ ተርጉሜዋለሁ፣ ለሚገኘው የትርጉም ስህተት አስቀድሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡

ይህ ታሪካዊ ደብዳቤ፣ ኢትዮጵያውያን የትም የተፈጨ ዱቄት እንደማንበላ በግልፅ የሚያሳይ ነውና ህፃናትም በቃላቸው ሊያጠኑት ይገባል፡፡

ኦክቶበር 9. 1995
ለክቡር ዶክተር ፒተር አ.ሽዋይዘር
የስዊዘርላንድ አምባሳደር
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ክቡር ሆይ
ምናልባት፣ (ደብዳቤዬን) በሼሊ “የፍቅር ሽሽት” መጀመሩ ተገቢ ሳይሆን አይቀርም፡፡
ፋኖሱ ሲተረከክ
          የአቧራ ላይ ብርሃን ያከትማል
ደመናው ሲበተን
          የቀስተ ደመናው ግርማ ይነጥፋል
ዋሽንቱ ሲሰበር
          ጣፋጭ ድምፆች ይተናሉ
ከንፈሮች ተናግረው ሲያበቁም
          የፍቅር ቃናዎች ይረሳሉ፡፡

ከአምባሰደሮች ሁሉ የላቁ የኢሰመጉ ወዳጅ እንደነበሩ አለመርሳታችንን (በቅድሚያ) ላረጋግጥልዎ እወዳለሁ፡፡ ቀደም ሲል የሞራል ድጋፍ እንዳደረጉልንም አልረሳንም፡፡ ለዚያም ውለታው አለብን፡፡

ከኢሰመጉ ጋር ያለዎት የቅርብ ግንኙነት ሳይሆን አይቀርም የትስስሩ ጥንካሬ በዚህ አጋጣሚ ለፈተና የተጋለጠው፡፡ ትስስሩም ደካማ መሆኑ በግልጽ ታወቀ፤ እንዲያም ሆኖ የመታውን ማእበል መቋቋም ተሳነው፡፡ ለመርህ የነበረንን አክብሮት ትተን በነበረን የጋራ ስሜት ምን ያህል መልካም እንደሠራን መገንዘቡ ከኛ ይልቅ ለክቡርነትዎ ግልፅ ነው፡፡ ክቡርነትዎ 10000 ዶላር የሚገመት ሃብት የማባከን ስሜት እንደተጫጫነዎ ያስታውቃል፡፡ ለዚህም የብክነት ስሜትዎ ማካካሻ ብሄራዊ ራታችንን፣ ሰብአዊ ክብራችንን እና ለመርህ ያለንን ተገዥነት እንድንሸጥልዎ ያደረጉት ሙከራ ምን ያህል እንዳስቆጣን ክቡርነትዎ ሊገነዘበው ይገባል፡፡ እንደ ሸክስፒር አባባል፣ ጣፋጭ ነገሮች በምግባራቸው ወደ ኮምጣጣነት ይቀየራሉ፡፡

በመንፈስ ደሃ እንዳልሆንን ክቡርነትዎ አይጠራጠሩም፡፡ ገንዘብዎን ለመመለስ ረዥም ጊዜ ስለወሰደብንም ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ውግዘት ከኢሰመጉ የባንክ መዝገብ ህገወጥ እገዳ ጋር ተጣምሮ መምጣቱን ክቡርነትዎ ያውቀዋልና፡፡ ሆኖም፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ከኢሰመጉ ጎን በመሰለፍ ገንዘቡን በሙሉ እንድከፍል ስላስቻለን ደስ ብሎናል፡፡ ቼኩን ከዚህ ደብዳቤ ጋር አያይዘን ልከናል፡፡

ከመልካም ምኞት ጋር
አክባሪዎ
መስፍን ወልደ ማርያም
የኢሰመጉ ሊቀመንበር

--------

አምሃ አስፋው በገብረክርስቶስ ደስታ ግጥሞች (መንገድ ስጡኝ ሰፊ) ላይ ካቀረቡት ዳሰሳ ላይ ከ”አንድምታ መጽሔት”  የተቀነጨበ /1999ዓ.ም/

ሰኞ 20 ሜይ 2013

የመጽሐፍ አዟሪዎች ቅሸባ ይቁም! - ኄኖክ ስጦታው


የመጽሐፍ አዟሪዎች ቅሸባ ይቁም

-
-
-
መጽሐፍት መደብር ሄደው መግዛት ለማይችሉ አንባቢያን አመቺ የገበያ አማረጮች ናቸው የመጽሐፍት አዟሪ ነጋዴዎች፡፡ እንደአነሳሳቸው መልካም ነበር፤ ብዙ መጻህፍትንም ገዝቻቸው አውቃለሁ፡፡ቅሸባቸውእንዲህ አፍጥጦ ሳይመጣ በፊት ነው ታዲያ፡፡ የመጽሐፉ መሸጫ ዋጋ እጅግ ጥንቃቄ በተሞላበት የማስመሰል ጥበብ 35 ብር የሚለውን ወደ 85 . . . .10ብር የነበረውን 40ብር፣ ባስ ካለም 100ብር የሚለውን 400 ብር በማድረግ የራሳቸውን የዋጋ ተመን አውጥተው እየተንቀሳቀሱ ያሉ ነጋዴዎች ጥቂት አይባሉም፡፡ በደራሲዎቹና አሳታሚዎቹ በወጣላቸው የዋጋ ተመን በቀላሉ ሊሰራጩ እና ሊነበቡ የሚገባቸው መጻሕፍት በዋጋ መፋረስ ምክንያት ብቻ ተደራሲ ጋር አለመድረሳቸው ትልቁ ችግር እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ዋናው ጥያቄመፍትሔው ምንድን ነው?? ምን መደረግ አለበት????”

አንዳንድ መጽሐፍ አዟሪ ነጋዴዎችን ባገኘሁት አጋጣሚ “ለምን ትክክለኛውን የዋጋ ተመን ተጠቅማችሁ አትሸጡም? ለምን ዋጋ ትጨምራላችሁ??” ብዬ ጠይቄ ነበር፤ መልሳቸው ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ነው ፤ “ ሰዉ ስለሚከራከር!” የሚል፤ ኧረ ምን ተሸለ?? ቁርጥ ዋጋ ድርድር አያሻውም፤ በተጻፈው የዋጋ ተመን መገበያት ካልቻለ ዋጋ ማሻቀብ ወይም መቀሸብ ፋይዳው እስከምን ድረስ ነው???

የመጽሐፍ አዟሪ ነጋዴዎችን መኖር እደግፋለሁ፡፡ ከሚነግዱት መጽሐፍ የሚያገኙት ትርፍ አነስተኛ እንዳልሆነም እረዳለሁ፡፡ አንድ መጽሐፍ አሳታሚ ለመጽሐፉ ማሳተሚያ ብቻ የሚያወጣው ገንዘብ ከመጽሐፉ ዋጋ አንጻር ሲሰላ 50% ያላነሰ ወጪ አለው፡፡ ይህ ወጪ መጽሐፉ ለሕትመት ቅድመ ዝግጅት የሚያወጣውን ብር አይጨምርም፡፡ /ቅድመ ዝግጅቱ ከሽፋን ምስል እስከ ጽሑፍ ትየባ ብሎም እስከ አርትኦት ይጓዛል/ ፡፡ ከባዱ ወጪ እና የትርፍ ክፍፍል ሂደት የሚያመራው ወደ መጽሐፍ አከፋፋዩ ሲያመራ ነው፡፡ አከፋፋዩ ከመጽሐፉ ዋጋ ላይ በጥቂቱ 35% ይቆርጣል፡፡ /በቀላል ሂሳብ ሲሰላ . . . 40ብር መጽሐፍ ላይ አከፋፋዩ 14ብር ይቆርጣል፡፡ 14ብሩንም ከመጽሐፍ አዟሪው ጋር የሚካፈለው ይሆናል/ ፡፡ የአዕምሮ ባለንብረቱ እና አሳታሚው ጥቅማቸው ምን ያህል ነው??? ይህ ጥቅማቸውንስ እንዴት ነው የሚያገኙት?

የእጅ በእጅ ሽያጭ በመጽሐፍ ነጋዴዎች ዘንድ የለም ለማለት እደፍራለሁ፡፡ እና ምንድነው ያለው?????? “ኮንሳይመንትአንዱ እና ባመዛኙ ገበያው የሚመራበት የቅብብል መንገድ ነው፡፡ ሲሸጥ የሚከፈል እንደማለት ነው/እዚህ ላይ ከተሳሳትኩ አርሙኝ/፡፡ አሁን ባለንበት የገበያ ስርዓት ደግሞ ደራሲው እንደ አሳታሚም ሆኖ ብቻውን የሚባክንበት ነው፡፡ ከኪሱ አውጥቶ ያሳተመውን መጽሐፍ ሽያጭ ትርፍና ኪሳራውን እንዳይለይ ከሚያደርጉት ትልቅ ችግሮች ዋንኛውም ስርዓት ይሄውሲሸጥ የሚከፈልበትግብይት ነው፡፡ አሁን ደግሞ እንዳይሸጥ ትልቅ እንቅፋት ተደንቅሮበታል፡፡ ችግሩም ግልጽ ነው፡፡ ከተመን በላይ ዋጋ የሚሸቅቡ ነጋዴዎች፣ ተሸጦ በሚከፈለው መጽሐፍ ላይ የራሳቸውን ዋጋ እየለጠፉም ሆነ እየቀሸቡ ችግሩን አባብሰውታል፡፡ ነገሩ ግልጽ እና የአደባባይ ዝርፊያ ከመሆኑም በላይ ድክድክ ለሚለው የአሳታሚው ዘርፍ እና ተቸግሮ በሚያሳትመው ጸሐፊው ላይ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖበታል፡፡
አዟሪዎቹ ሕጋዊ እንዲሆኑ ወይም ሕገወጥ የዋጋ ቅሸባ እንዲቆም ጉዳዩ ይበልጥ የሚመለከተው አካል /የኢትዮጵያ ደራሲያን ማሕበር / ምን አይነት እንቅስቃሴ አድርጓል/   … ሌሎች መሰል ተቋማትስ ምን እየሰሩ ነው