ረቡዕ 3 ኦክቶበር 2012
ሰኞ 1 ኦክቶበር 2012
ሞክሼ የአማርኛ ፊደላት እና የባለሙያዎች ማብራሪያ ክፍል ሁለት
ሞክሼ የአማርኛ ፊደላት
እና
የባለሙያዎች ማብራሪያ
ክፍል ሁለት

የሄኖክ ስብስብ(henoksitotaw65@gmail.com)
ታህሳስ 2005ዓ.ም
ውድ አንባቢዎች፤ ከዚህ በታች የምታነቡት ሀሳብ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ላይ የተነበቡ ሲሆን ምንጫቸውም ከየመጣጥፎቹ ግርጌ ይገኛል፡፡ ለዚህም ነው “ስብስብ” በሚል ለመግለፅ የተገደድኩት፡፡ በስብስብ መጣጥፎቹ ላይ የጨመርኩት አንዳች ነገር የለም፤ ምክንያቱም አላማዬ በሞክሼ ፊደላት እና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ለመበየን ሳይሆን፣ እንደኔው ግራ ለተጋቡት ማጋራት ነውና፡፡
-5-
በዲ/ን ኅሩይ
ባየ
.
. .ኢትዮጵያ ከምትታወቅባቸው ዐበይት ሀብቶቿ ውስጥ አንዱ የራሷ የሆነ ፊደልና ቋንቋ እየተጠቀመች ለትውልድ ስታስተምር መኖሯ
ነው፡፡ ለዚህም የፊደል፣ የቋንቋ ዕድገትና ሥልጣኔ ከፍተኛውን ድርሻ የምትይዘውና በር ከፋቿ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ቤተ ክርስቲያን ዛሬም እንደ ጥንቱ የሆሄያቱ ታሪክ እንዳይረሳ መልክአቸው እንዳይጠፉ ለትውልዱ
ታስተምራለች፡፡ ስለሆነም በዘንድሮው የመስቀል በዓል በመስቀል ዐደባባይ አራቱ ሆሄያት እንዳይረሱ ትኩረት እንደሚያሻቸው ጥሪ
ቀርቧል፡፡
ሆሄ የሚለውን ቃል ፊደል ተብሎ ሲነገር እንሰማለን፤ በጽሑፍም እናነባለን፡፡ ፊደልን ፈደለ
ጻፈ ካለው የግእዝ ግስ አውጥተን ጽሑፍ የሚለውን ትርጉም እናገኛለን፡፡ በሌላ አተረጓጐም ፊደል የሚለው ግስ ጠብቆ ሲነበብ
ፈጠረ የሚለውን ትርጉም ያስገኛል፡፡ ፊደል ፈጣሪ /መፍጠሪያ/ መባሉም ቃላትን ስለሚያስገኝ ነው፡፡ አባቶቻችን “ዘእንበለ ፊደል
ኢይትነገር ወንጌል.. ያለፊደል ወንጌል አትተረጐምም” ማለታቸው ለመጻፍም ሆነ ለማንበብ፤ ለመተርጐምም ሆነ ለማመስጠር ፊደላት
ጉልሕ ድርሻ እንዳላቸው ሲያመለክቱ ነው፡፡
እሑድ 30 ሴፕቴምበር 2012
ሞክሼ የአማርኛ ፊደላት እና የባለሙያዎች ማብራሪያ ክፍል አንድ
ሞክሼ የአማርኛ ፊደላት
እና
የባለሙያዎች ማብራሪያ
ክፍል አንድ
የሄኖክ ስብስብ
ታህሳስ 2005ዓ.ም
እና
የባለሙያዎች ማብራሪያ
ክፍል አንድ
የሄኖክ ስብስብ
ታህሳስ 2005ዓ.ም
{PDF}
ውድ አንባቢዎች፤ ከዚህ በታች የምታነቡት ሀሳብ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ላይ የተነበቡ ሲሆን ምንጫቸውም ከየመጣጥፎቹ ግርጌ ይገኛል፡፡ ለዚህም ነው “ስብስብ” በሚል ለመግለፅ የተገደድኩት፡፡ በስብስብ መጣጥፎቹ ላይ የጨመርኩት አንዳች ነገር የለም፤ ምክንያቱም አላማዬ በሞክሼ ፊደላት እና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ለመበየን ሳይሆን፣ እንደኔው ግራ ለተጋቡት ማጋራት ነውና፡፡
ውድ አንባቢዎች፤ ከዚህ በታች የምታነቡት ሀሳብ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ላይ የተነበቡ ሲሆን ምንጫቸውም ከየመጣጥፎቹ ግርጌ ይገኛል፡፡ ለዚህም ነው “ስብስብ” በሚል ለመግለፅ የተገደድኩት፡፡ በስብስብ መጣጥፎቹ ላይ የጨመርኩት አንዳች ነገር የለም፤ ምክንያቱም አላማዬ በሞክሼ ፊደላት እና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ለመበየን ሳይሆን፣ እንደኔው ግራ ለተጋቡት ማጋራት ነውና፡፡
-1-
የፊደል
ዘር ይጠበቅ ባህሉም ይከበር
በፊታውራሪ አበበ ሥዩም ደስታ
በፊደሎቻችን ላይ ሦስት ሀ - ሐ - ኀ፣ ሁለት አ - ዐ -፣ ሁለት ሠ - ሰ ሁለት፣ ጸ - ፀ አሉ፡፡ እነዚህ ፊደሎች የራሳቸው የሆነ የስም አጠራርም አላቸው፤ ሀሌታው ሀ፣ ሐመሩ ሐ፣ ብዙኃን ኀ፣ ንጉሡ ሠ፣ እሳቱ ሰ፣ ጸሎት ጸ፣ ፀሐዩ ፀ ይባላሉ፡፡ በጽሑፍ የሚገቡበትን ተገቢ (ተስማሚ) ቦታም አላቸው፡፡ ለምሳሌ በሁለት ፊደሎች መጠቀም ይቻላል፡፡ ሀገር አገር ይህ ትክክለኛ አጻጻፍ ሲሆን፤ ነገር ግን ከዚህ ውጪ ሐገር፣ ኀገር ብሎ መጻፍ ግን ስሕተት ይሆናል፤ የሚከተሉትን ደግሞ እንመልከት፤ ሕገ መንግሥት፣ ሕገ ወጥ፣ ሕዝብ፣ ሕብረት፣ ዓቃቤ ሕግ፣ ወዘተ. የመሳሰሉት አጻጻፋቸው ትክክል ነው፡፡ ከዚህ ልማዳዊ አሠራር ውጪ ህገ መንግሥት፤ ህገወጥ፤ ህዝብ፤ ህብረት፤ አቃቤ ህግ ስሕተታዊ አጻጻፍ ይሆናል፤ ሌላ ማስረጃ ቢፈለግ፤ ኃይለሥላሴ የሚለው ስም ሦስት የተለያዩ ፊደሎች ይዟል፡፡ የመጀመርያው ፊደል ብዙኀን - ኃ - ሲሆን፣ ከንጉሡ -ሥ- ሳድስ፣ ከእሳቱ -ስ- ሃምስን በመጻፍ እንዲካተት ተደርጓል፡፡ ሀይለ ስላሴ ብሎ ቢጻፍ ግን የፊደሎቻችን የአጻጻፍ ሥርዓት ማፋለስ ይሆናል፤ በአቦ ሰጡኝ ፊደሎቻችን አለቦታቸው መግባትም፣ መጻፍም የለባቸውም፡፡
በዓፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት በማስታወቂያ ሚኒስቴር ረዳት ሚኒስትር የነበሩት የተከበሩ ብላታ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ የቅድሚያ ዓይነተኛ ሥራቸው የፊደሎች ዘሮች አለቦታቸው እንዳይጻፉ መጠበቅ ነበር፤ በዚያን ወቅት ተማሪ ሁኜ አልፎ አልፎ በጋዜጣ እንዲወጣልኝ አንድ አንድ ሐሳብ በማመንጨት እጽፍ ስለነበር ብዙ ጊዜ አርመውኛል፡፡
ከእሳቸው በተማርኩት ትምህርትና ባገኘሁት ልምድ አእምሮዬን አሻሽያለሁ፡፡ በቀድሞው የንጉሠ ነገሥቱ ዘመነ ሥርዓት የክፍል ሹም የመጀመርያ ሹመት ሆኖ ወደ ላይ እንደሚከተለው ይዘልቃል፡፡ ዲሬክተር ዋና ዲሬክተር፤ ረዳት ሚኒስትር ምክትል ሚኒስትር፣ ሚኒስትር ዲ-ኤታ፤ ሚኒስትር፡፡ ከምክትል ሚኒስትር ወደ ላይ ያሉት እስከ ሚኒስትር ማዕረግ የደረሱት ክቡር ይባላሉ፡፡ ከዚህ በታች ያሉትን ግን ክቡር አይባሉም፡፡ በተመሳሳይ ያሉትን ማለት ኮሚሽነሮች፤ ሌ/ጀኔራሎች፣ አምባሳደሮች ክቡር ይባላሉ፡፡ ሚኒስትሮች የነበሩ በዳሬክተርና በሥራ አስኪያጅነት ሥራ ቢመደቡ እንኳን የቀድሞውን የሚኒስትር ማዕረጋቸውና ክብራቸው አይቀነስባቸውም፡፡ ክቡር መባል አለባቸው፡፡ ሥርዓት ነውና፡፡ ይህንኑ መለመድ ይገባዋል፤ በወታደሩ ሹመት አሰጣጥ ግን ያለው ሥርዓት የተጠበቀ ስለሆነ መልካም ነው እላለሁ፡፡ ከዚሁ ሌላ የምለው አለኝ፡፡ ባሁኑ በኢሕአዴግ መንግሥት ዘመን አምባሳደር ነዋሪ የማዕረግ መጠሪያ ስም ሆኖአል፡፡ አንድ አምባሳደር የዲፕሎማሲውን ሥራ አቁሞ ሲዛወር ልክ በሥራው እንዳለ ተቆጥሮ “አምባሳደር” እየተባለ መጠራት የለበትም፡፡
ለምሳሌ በዓፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት አምባሳደርነት ተሹመው የነበሩት ክቡር አቶ ጋሻው ዘለቀ፣ ክቡር አቶ ዘነበ ኃይለ፣ ክቡር ልጅ መንበረ ያየህ ይራድ፤ ክቡር ፊታውራሪ መሐመድ ሲራጅ ብዙ ዘመን በአምባሳደርነት ሲሠሩ ቆይተው ተልእኮዋቸውን ፈጽመው ወደ አገራቸው ሲመለሱ አምባሳደር የሚል ቀርቶ በቀድሞ ስማቸው አቶ ተብለው ነበር የሚጠሩት፤ ይህንኑ ጠይቆ ለማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ፊታውራሪ የነበሩትም፤ ፊታውራሪ ተብለው ይጠራሉ፡፡ ዘላቂ ሆኖ ከሰው ጋር ቅጽል የማዕረግ ስም ሆኖ የሚያገለግል ነው፡፡ በራሴ ምሳሌ ልውሰድ፤ ከግርማዊ ጃንሆይ በአዋጅ የተሰጠኝ የማዕረግ ስም ፊታውራሪ ነው፤ በዚህ ምድራዊው ዓለም እስካለሁ ድረስ የምጠራበት ሲሆን፣ ከሞትኩም በኋላ እጠራበታለሁ፡፡ እንዲሁም በንጉሠ ነገሥቱ መልካም ፈቃድ የሚሰጠው የሥልጣንና ማዕረግ ተዋረድ ባላምባራስ፣ ግራዝማች፣ ቀኛዝማች ፊታውራሪ፣ ደጀዝማች፣ ቢትወደድ፣ ራስ ቢትወደድ፣ ልዑል ራስ፣ አልጋ ወራሽ፣ ንጉሥ ንጉሠ ነገሥት ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ብላታ፣ ብላቴን ጌታ፣ ፀሐፊ ትዕዛዝ፣ ሊቀ መኳስ በሕይወት ሳሉ ይጠሩበታል፡፡ ከሞቱም በኋላ ስማቸውና ታሪካቸው በተነሣ ቁጥር ከመቃብር በላይ ሆኖ በማዕረጉ ስም ይጠሩበታል፡፡
ሐሙስ 27 ሴፕቴምበር 2012
ቅዳሜ 22 ሴፕቴምበር 2012
እስረኞቹን ፍቺ !
እኔ ዛሬ ምኒልክን ስለምን አደንቀዋለሁ ?
ከቶ ለምን አብዲስ አጋን - ጐበናን አወድሳለሁ ?
ስለምን ገረሱ ዱኪን - ካዎ ጦናን አነሳለሁ ?
ከእንግዲህ ለአያ በላይም - ለቋረኛውም አልዘፍንም
ለሰሜኑ ልጅ አሉላ ያማረ ቅኔ አልቀኝም
ኃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ በእርስዎ ስምም አልፎክርም
እኔ የገብርዬ ባርያ! የአባ ጅፋር ልጅ አልልም !!
አልልም! ከቶም! አልልም!
አይኔን ወደፊት ነው እንጂ ወደኃላዬስ አልጥልም!!
ከእንግዲህ ኩራት ፍለጋ አልሄድም ወደትላንቱ
ከገዛ ትውልዴ መሀል ተገኝታለች አንዲት ‘ብርቱ’
ለምን ወደኃላ ሄጄ ሙታን እቀሰቅሳለሁ?
አዲስ ኮከብ ስትወለድ በአይኔ ብረቱ አይቼአለሁ!!
ዛሬማ ልቤን ሞልቼ ፣
ዛሬማ ታሪክ አይቼ ፣
የግንቦት ጭጋግ ደመናን፣ ጨለማን የተቃወመች
ይኸው አዲስ አበባ ላይ አዲስ ኮከብ ተወለደች
ሎሚ መቼም መድሃኒት ነው፣ ማንጐም - ትርጐም ደስ ይላል
ግና ከፖም - ከመንደሪን ብርቱካንን ያህል የታል ?
የታል? የታል? የታል? የታል?
ከስንቱ ጥሬና ብስል ብርቱካንን ያህል የታል?
ዓርብ 21 ሴፕቴምበር 2012
Dr Kebede Michael's poetry book ታሪክና ምሳሌ ፪ /tarik ena mesale/ part 2 in [PDF]
Dr Kebede Michael was one of the giants in the field f education and literature in Ethiopia. He wrote a total of 26 books including a wide range of translations from various languages. From 1940 to1970, he wrote Amharic school textbooks in which he provided generations of Ethiopian students with enlightening ideas about a wide range of issues and disciplines.
His writings were in both prose and poetry and his poems follow rhyming and writing styles of his own. He also translated - among many - Romeo and Juliet, as well as Macbeth of William Shakespeare. Kebede Michael’s literary works reflect many shades of character and behavior of the Ethiopian society. The contents of many of his books are on history, education, development, philosophy, religion, science and so on.
He worked as an inspector in the Ministry of Education, as Deputy Director in the Ministry of Foreign Affairs (1942), as Director of the National Library (1944), as Director General of the Ministry of Education, and as a Cabinet Minster in the Imperial Palace. He was also delegated to many international conferences including at the United Nations in New York.
He received the first Prize for Literature from Emperor Haileselassie. He also received awards from governments of France, Germany, Italy, USSR and Mexico. And in 1990, he received an Honorary Doctorate Degree from Addis Ababa University for his unparalleled excellence in literature as well as for inspiring generations of Ethiopian authors and writers.
Dr. Kebede Michael died on 12 November 1998 at the age of 82. No other Ethiopian in the country’s history so far has been able to write as extensively on a wide variety of disciplines as did Kebede Michael.
His contributions are enormous to the development of education and literature. And he may be deceased, yet his legacy will live on forever; and Ethiopians are greatly thankful to him.
ታሪክና ምሳሌ ፪ በከበደ ሚካኤል ከተደረሱት ሁለት ክፍል ታሪክና ምሳሌ መጽሃፎች ሁለተኛው ክፍል ነው። መጽሃፉ ስለ ሃገርና ቀን ተቀን አኗኗር ዘይቤወች ምክሮችን በምሳሌ የሚያቀርብ ነው።
TARIK ENA MESALE 2
|
Dr Kebede Michael's poetry book ታሪክና ምሳሌ ፩ /tarik ena mesale/ part one in [PDF]
Dr Kebede Michael was one of the giants in the field f education and literature in Ethiopia. He wrote a total of 26 books including a wide range of translations from various languages. From 1940 to1970, he wrote Amharic school textbooks in which he provided generations of Ethiopian students with enlightening ideas about a wide range of issues and disciplines.
His writings were in both prose and poetry and his poems follow rhyming and writing styles of his own. He also translated - among many - Romeo and Juliet, as well as Macbeth of William Shakespeare. Kebede Michael’s literary works reflect many shades of character and behavior of the Ethiopian society. The contents of many of his books are on history, education, development, philosophy, religion, science and so on.
He worked as an inspector in the Ministry of Education, as Deputy Director in the Ministry of Foreign Affairs (1942), as Director of the National Library (1944), as Director General of the Ministry of Education, and as a Cabinet Minster in the Imperial Palace. He was also delegated to many international conferences including at the United Nations in New York.
He received the first Prize for Literature from Emperor Haileselassie. He also received awards from governments of France, Germany, Italy, USSR and Mexico. And in 1990, he received an Honorary Doctorate Degree from Addis Ababa University for his unparalleled excellence in literature as well as for inspiring generations of Ethiopian authors and writers.
Dr. Kebede Michael died on 12 November 1998 at the age of 82. No other Ethiopian in the country’s history so far has been able to write as extensively on a wide variety of disciplines as did Kebede Michael.
His contributions are enormous to the development of education and literature. And he may be deceased, yet his legacy will live on forever; and Ethiopians are greatly thankful to him.
|
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)


