2013 ጃንዋሪ 12, ቅዳሜ

ወንድ ብቻውን ነው እሚያለቅስ- ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን



ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ      
ተሸሽጎ ተገልሎ፥ ተሸማቆ ተሸምቆ
ከቤተ-ሰው ተደብቆ
መሽቶ፥ የማታ ማታ ነው፥ ሌት ነው የወንድ ልጅ እንባው
ብቻውን ነው የሚፈታው፡፡ . . .
ብቻውን ነው የሚረታው፡፡ . . .
ችሎ፥ ውጦ፥ ተጨብጦ፥ ተማምጦ ተጣጥሮ
በሲቃ ግት ተወጥሮ
እንደደመና ተቋጥሮ
እውስጥ አንጀቱ ተቀብሮ . . .
መሽቶ፥ ረፍዶ፥ ጀምበር ጠልቆ
የጨለማ ድባብ ወድቆ
በእንቅልፍ ጥላ ሲከበብ፥ በዝምታ ሲዋጥ አገር
ፍጡር ሁሉ ተስለምልሞ፥ ብቸኝነት ብቻ ሲቀር . . .

2013 ጃንዋሪ 10, ሐሙስ

እግር እንይ! (ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን)


poem in pdf
እግር እንይ!
(ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን)

አርቀን ማስተዋል ማለት፣ የኛን ሥልጣኔ ድልድይ
እግር ማየት ነው ብለዋል፣ እስቲ እንግዲህ እግር እንይ!
            ያባቶችህ ያይን ድንበር፣ ከተረከዘ ሎሚ ሳያልፍ
            አንተ ግን ጆቢራው-ዘራፍ
ጠፍር አይወስንህ ጉብል
ጥሎ በዘመንህ ዕድል
ዓይንህ ባት አልፎ እንዲዋልል፤
ቴህ ወዲያ ጀግንነት የለ፣ ተዚህ የከረረ ግዳጅ
ባደባባይ የዱር ገደል፣ ስትናደፍ የእግር አዋጅ
ሌሊቱን በየሌት- ‘ግለብ’፣ ቀኑን ጭምር በጠራራ

2013 ጃንዋሪ 7, ሰኞ

አደፍርስ - የብዕር ጠብታ /ከባለፈው የቀጠለ/



ሙሉውን ለማንበብ
አደፍርስ - የብዕር ጠብታ 

(ከባለፈው የቀጠለ)

ቅንጣቢ ዳሰሳ ፡-ሄኖክ ስጦታው

              ****** ******      ****** *****

አደፍርስ የብዕር ጠብታ ነው፡፡ የጥበብ መታያ - የእውነት መገለጫ ነው፡፡ ድብቅ ሰብእና የለውም፡፡ የገፀ-ባህሪው ውስጠ ምስል ግልፅነት የተከተለ ነው፡፡ የአገራችን ደራሲያን ለዋና ገፀባህሪይ ነፃነት ለመስጠት የሚጠቀሙበት ተመሳሳይ የአሳሳል ስልት በአደፍርስ ላይ መስተወሉን ልብ ይለዋል፡፡

“ቀልድ ጨዋታ የማላዘወትር፣ የተሰማኝን ሃሳብ ያስቀይማል አያስቀይምም ብዬ ሳላስብ ቀጥታ መግለፅ የምወድ…” ገፅ129 እያለ እራሱን የገልጸዋል፡፡ ከደራሲው አንፃር ስለ አደፍርስ ግልፅ ባህርይ  የነገረናል፤ “የማይቦዝን ፣ ስለውጤቱም እምብዛም የማያስብ፣ እንደልቡ የሚናገር፤ ተቃዋሚዎቹም ከራስ ፀጉሩ የበዙ ናቸው…”
ዳኛቸው ወርቁ ለአደፍርስ እንደልቡ የመናገር ነፃነትን በመስጠት፣ የራሱን ነፃነት እንዳወጀ እናስተውላለን፡፡ እውነታውም ይህ ነበር፡፡ የወቅቱን ስርአት፣ ስርአቱ ለዘመናት የፈጠረውን ተፅዕኖ፣ ጭቆና እና ብዝበዛ ብሎም አጉል ልማዶችን በአደፍርስ አማከኝነት አውግዟል፡፡ በደራሲው ውስጥ አደፍርስ አለ፤ በአደፍርስ ውስጠም ደራሲው ፡፡

መጽሐፉ፣ በተማረው እና ባልተማረው ማህበረሰብ መሀል ለውን ለውጥ ያሳያል፡፡ ስለመሀይምነት መጥፋት ያትታል፡፡ አደፍርስ ለኢትዮጵያ  ያለውን ብሩህ ተስፋ ትምህርትን አስታኮ ይናገራል፡፡ መዕራፍ 26 ለዚህ ዋቢ የሚሆን ነው፡፡ የምዕራፉ ውይይት አደፍርስ በመጨረሻዎቹ ምዕራፍ ለያዘው ሥራ መጠቆሚያም ጭምር ሆኗል፡፡

“ሀዲስ” እና “አደፍርስ”   

አደፍርስ በዓሉ ግርማ የደረሰው “ሀዲስ” ረጅም ልብ ወለድ ዋና ገፀ ባህርይ ሀዲስ  ላይም  የባህርይ ተፅዕኖ ያሳደረ