ተጠየቁ
ዳኞች!
~በ
ኄኖክ ስጦታው —
ችሎት
እንዴት ዋለ?!
ማን ተፈረደበት?!
ማንስ ተቀጠረ?!
ይህ
ሁሉ እስረኛ ወኅኒ የታጎረ
በፍርዱ
ረካ?! ወይስ
ተማረረ?!
ተጠየቁ
ዳኞች! መልሱልኝ እውነት….
የነገር
ግራ ቀኝ፣ የምትመረምሩት
ግዜው
ምን ያህል ነው?! ቀናት
ወይስ ሳምንት?!
ዓመት
ሁለት አመት?!
ሰምታችሁ
ምትፈርዱት?!
ይግባኝ!
ይግባኝ!
ይግባኝ!
ይግባኝ
ደረጃ አንድ፣ ይግባኝ ከፍተኛ
ይግባኝ
ዐቃቤ ሕግ፣ ይግባኝ ሰሚ ዳኛ!
ተጠየቁ
ዛሬ፣ መልሱልኝ እውነት
ግዜ
አላችሁ ወይ ሰምታችሁ ለመፍረድ?!
ምን
ያህሉ ሰው ነው ወኅኒ የተጣለ?!
ሰሚ
ጆሮ አጥቶ ፍትህ ያልታደለ፡፡
ባላጠፋው
ጥፋት በሀሰት ውንጀላ
ክርክር
ረትቶት የአግቦ ፍተላ
“ይግባኝ!”
ብሎ ሲጮኽ፣ “ልስማኽ” የማይሰኝ
ምን
ያህል ነፍስ ነው፣ ወኅኒ ውስጥ የሚገኝ?!
ይግባኝ!
ይግባኝ!
ይግባኝ!
ይግባኝ
ደረጃ አንድ፣ ይግባኝ ከፍተኛ
ይግባኝ
ዐቃቤ ሕግ፣ ይግባኝ ሰሚ ዳኛ!
“ሀ
-ሞት” የግጥም መጽሐፍ
—ኄኖክ ስጦታው —
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ