ቅዳሜ 3 ሜይ 2014

የ“ሸኖ ቤት ሃሳቦች” #ኄኖክ_ስጦታው



ሸኖ ቤት ሃሳቦችየማንበብ ሱስ የተጠናወተኝ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳለሁ ነበር፡፡ በርግጥ ብዙዎቹ ሃሳቦች በጨዋ ቋንቋፀያፍተብለው የሚነገሩ ቢሆንም ብሶትና ምክርን በጨዋ ገለፃ የሚቀርቡ ሃሳቦችም አይታጡም፡፡ ያም ሆኖ ሕዝብ የሚጠቀምባቸው መፀዳጃ ቤቶች ስገባ በግድግዳው ላይ የተጻፉ ጽሑፎችን ማንበብ ያዝናናኛል፡፡

ሸኖ ቤትን ለመውደድ የፎክሎር ተማሪ መሆን አይጠይቅም፡፡ ከማይረቡ መፅሐፍት የተሻለ ምልከታን እና ሂዩመርን በሸኖ ቤት ሃሳቦች መቃረሜ በራሱ ለመፀዳዳት የማባክነውን ጊዜ የሚክስ ቁምነገር አላጣበትምና፡፡

የዘርሲዎች ፍቅርየተሰኘው ልቦለድ መፅሃፍ ላይ አንድ ገፀባሕርይ አስታውሳለሁ፡፡ በተለይ መፀዳጃ ቤት ስገባ ብዙ ጊዜ ትዝ ይለኛል፡፡ (አብሮኝ ይገባል - - ብል ይቀላል፡፡) ይህ ሰው ቁምነገርን የሚቃርመው ከመፀዳጃ ቤት ነው፡፡ ግድግዳ ላይ የሚጻፍ ግራፊቲ አልነበረም የሚያነበው፡፡ ሰዎችካካቸውንየጠረጉበትን ወረቀት ሰብስቦ ኪሱ በመክተት እና በማንበብ ነበር፡፡

እነዚህ የግድግዳ ላይ ጽሁፎች ስለምንስ ይጻፋሉ? ግባቸው ምንድነው? ... ምክንያቱን እርሱት፡፡ ከየት መጡ የሚለው ምርምር አያሳስበኝም፡፡ ባለቤት አልባነታቸው በራሱ በቂ ምክንያት ነው፡፡ ምክንያት ከስም ይጀምራልና፡፡ ማንነቱን ለማወጅ የመፀዳዳት ባህሉን አደባባይ ላይ ከሚፈጣጥም ሰው ምንም አልጠብቅም፡፡ ማንነቱን በመጸዳጃ ቤት ግድግዳ ላይ የሚያሰፍር ማንነቱ ያልታወቀ ሰው ግን ታዳሚ ነኝ፡፡ (እስቲ ዛሬ የተመረጡ ትውስታዎቼን በሹካ ጨልፌ ላካፍላችሁ፡፡)

ለመጀመሪያ ጊዜ ካነበብኳቸው ውስጥ የሚመደብ የመፀዳጃ ቤት ሃሳብ እንዲህ የሚል ነበር፡-

“God is dead!” -Nietzshce
“Nietzshce is dead!” -God

ያኔ ይህን ሳነብ ያልገባኝ ብዙ ነገር ነበር፡፡ በርግጥ ኒቼእግዚአብሔር ሞቷልበሚለው ግንዛቤው ዛሬም ድረስ (ሞቶም) ያወዛግባል፡፡ በሕይወት በነበረበት ጊዜእግዚአብሔር ሞቷል ሰዎችም ነፃ ወጥተዋል...” እያለ መስበኩን የተረዳሁትም ከጥቅሱ በኋላ ነበር፡፡ አመታት አልፈው፡፡ የኒቼን ሞት ጠብቆ እግዚአብሔር እንዲህ ማለቱን ግን መፀዳጃ ቤት እንደ ትንቢት ቀድሞ አሳውቆኛል፡፡ ጥበብ ከጲላጦስ መፅሐፍ ላይ ይህን ጥቅስ ሳነበው አልደነቀኝም፡፡ ጥቅሱን ሲያስታውሰኝ ግን የሆነ ነገር ግን ሸቶኝ ነበር፡፡ ያም ጠረን፣ ይህን አባባል ያነበብኩበት መፀዳጃ ቤት አጉል ጠረን ነበር፡፡

በአንድ ኮሌጅ መጸዳጃ ቤት ውስጥ ደግሞ እንዲህ የሚል መልዕክት ግድግዳው ላይ ተፅፎ አነበብኩ፡- “ምን ግድግዳው ላይ ታፈጣለህ!? አርፈህ አትፀዳዳም!?” ሆሆሆ... ሰዉ ጨምሯል!

በሌላ ዩኒቨርስቲ መፀዳጃ ቤት ውስጥም እንዲህ አይነት ትዕዛዝ አጋጥሞኝ እንደነበር አልረሳውም፡፡ በደቃቅ ጽሑፍ የተጻፈ መልዕክት ከመጸዳጃው በር ላይ ሰፍሮ አየሁና ከቅምጤ በመጠኑ ብድግ ብዬ ላነብ ስሞክር ያገኘሁት መልዕክት አስደንግጦየሚያስቀምጥነበር፡፡ሃሳቡ እንዲህ የሚል ነበር፡- “ሰው ማለት አንተ ነህ፡፡ አሁን ወደነበርክበት ተመልሰህ አርፈህ እራ! ” የሚል ትዕዛዝ ፡፡

የሸኖ ቤት ግድግዳ ላይ ከተፃፉ ሃሳቦች ሌላው የማርከኝ እንዲህ የሚል ነው -

ቺክህን ጥሩ ነገሮች እንዴት እንደምታሳያት በማሰብ አትጨናነቅ፡፡ አሁን እየጣልክ ያለውን እንቁላል ግን ጠብሰህ እንዳታበላት አደራ! ስትጨርስ ውሃ ድፋበትና ከሌሎች እይታ ሰውረው!”

የሸኖ ቤት ግድግዳ ሃሳቦች አንዳንዴም ፍልስፍና ይቃጣቸዋል፡፡ በአንድ የሕዝብ መፀዳጃ ቤት ውስጥ ያነበብኩትሃሳብ ለዚሁ ምስክር ነው፡፡ እንዲህ ይላል፡-

[“መኖር ማለት፣ በምታባክነው ጊዜ የምታጣው ብኩንነት ነው፡፡ ለመኖር ስትል ከምታባክናቸው ሰዓታት ትልቁን ቦታ የሚይዘው ምን እንደሆነ ታውቃለህ?”

አውቃለሁካልክ ተሳስተሃል! በዚህ ሰዓት ማራት አልነበረብህም!!”]

ትውስታዬን ተደብቄ በተጠቀምኩበት የሴቶች መጸዳጃ ቤት ግድግዳ ላይ ባነበብኩት ልቋጭ፡፡


በወንዶች ከሚነገሩ - ውሸቶች መሃከል የማላምነውሮም በአንድ ቀን አልተገነባችምየሚሉትን ብቻ ነው፡፡


(›››› ሌሎች ጽሑፎችን በፌስቦክ ገጽ ለማንበብ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ፡-  https://www.facebook.com/pages/የኄኖክ-diary/736486173038263

ረቡዕ 16 ኤፕሪል 2014

የኄኖክ-diary (በፌስቡክ ተከፈተ፡፡)


ውድ የእልፍኜ ታዳሚያን፤ የኄኖክ-diary በፌስቡክ መንደር የከፈትኩት አዲሱ ገጼ ነው፡፡

የኄኖክ-diary
የኄኖክ-diary
ማነው ዳየሪዬን ማንበብ የሚፈልግ?  የኄኖክ-diary ፡-  https://www.facebook.com/henokspad በዚህ ሊንክ ገብተው ላይክ በማድረግ ይከተለኝ፡፡

ሰኞ 14 ኤፕሪል 2014

የበዓል ሰሞን ፍተላዎች - ኄኖክ ስጦታው



በግ ከመግዛት በግ የገዛንባቸውን ዘመናት በማሰብ መፈተል ይቀላል፡፡ 

ፍተላ 1 (እውነተኛ)

ለአዲስ ዓመት ቅበላ ሸመታ በወጣንበት ባንዱ የሆነ ነው፡፡ ሶስት ሆነን ገበያ ወጣን ፡፡ ሁለታችን ሙክት ስንገዛ ሶስተኛው ጓደኛችን ደግሞ እኛ አንድ ሙክት በገዛንበት ሂሳብ ሁለት ትንንሽ በጎችን ሸመተ፡፡ ሊቀልባቸው ነው ሊቀለባቸው?¡? . . . ለምን ሁለት ትንንሽ በጎች እንደገዛ ጠየቅነው፡፡ በኩራት ነገረን፡፡

እቅዱ እንዲህ ነው፤ አንዱን ለዘመን መለወጫ ይባረካል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ለቅዱስ ዮሐንስ፡፡ 

በቃ! የሸመታ ጥበቡ አሪፍ ቅጽል ስም አሰጠው፡፡ቬንገርተባለ፡፡

በሌላ ቀን . . .

ባለ ሁለት በጉን ሰው (“ቬንገር) በአካል የማያውቁ የኔ ጓደኞች ሁሉ ስለሆነው ተረኩላቸው፡፡ አብርሃም ጆሮ ደረሰ፡፡ አብርሃም ዛሬ የነገርከውን ቀልድም ይሁን ቁምነገር ሪሚክስ አድርጎ በሌላ ቀን መልሶ ለራስህ ይነግርሃል፡፡ ማን እንደነገረው ቢረሳም የተነገረውን የማይረሳ ጓደኛ ኖሮህ አያውቅም? እንደዚህ አይት ሰው ነው፡፡ 

ለገና በዓል ዋዜማ አብርሽ አብሮኝ ገበያ ወጣ፡፡ቬንገርምነበር፡፡ የበግ ወሬ ተነሳ፡፡ 

አንዱ የተባለውን ልንገራችሁ . . . ” ብሎ ወሬ ጀመረ፡፡ አብርሽ፡፡አንድ ትልቅ በግ በሚገዛበት ገንዘብ ሁለት ትናንሽ በጎች ገዝቶ ቤቱ ሲገባ ምን እንዳሉት ታውቃላችሁ ??!! . . .”

እኔናቬንገርተፋጠጥን፡፡ አብርሽ ወሬውን ቀጠለ፡፡ እስኪጨርስ ታግሼ እንዲህ አልኩት፡-

እሱ ነውቬንገር፡፡ ተዋወቀው፡፡

አብርሽ ደነገጠ፡፡ ድንጋጤው ደግሞ እኛን አሳቀ፡፡ ከሳቁ በኋላቬንገርወደጆሮዬ ተጠግቶ፡-

በስሜ ካልጠራኸን ጓደኛዬ አይደለህም!” አለ፡፡ እንዳለኝም አደረኩ፡፡ (በተቃራኒው ይህን ወሬ ስጽፍ እውነተኛ ስሙን አልጠራሁም፡፡)

የዛን እለትቬንገርትልቅ በግ ገዛ! አብርሽ ግንቬንገርገዝቷቸው ከነበሩ ትናንሽ በጎች ያነሰች በግ ገዛ፡፡

ቬንገርበተራው - 

በግ ገዛሁ እንዳይል ንገረው፡፡ የበግ ለምድ የለበሰች ዶሮ ገዛሁ ይበል፡፡ 

ፍተላ 2 (በእውነት የሆነ)

እንዲሁ በሌላው በዓል . . . ሁለት ሆነን በግ ሸመትን፡፡ ዶሮ ማነቂያ የምናውቀው አንድ ሌላ ወዳጃችን ድክም ያለች በግ እንደ ቦርሳ አንጠልጥሏት መጣናበፒያሳ የምታልፉ ከሆነ እባካችሁ ሸኙኝአለን፡፡ ተባበርነው፡፡ የእርሱ በግ ከሁለት ቀንዳም በግ መሐል የመኪና ኪስ ውስጥ አስገባንና ጉዞ ተጀመረ፡፡ መንገድ ላይ በመኪና ኪሱ ውስጥ የጦፈ የመንጓጓት ድምጽ ተሰማ፡፡ ያው የተለመደ የበጎች መንፈራገጥ እንደሆነ በማሰብ ፒያሳ ደረስንና መኪናው ቆመ፡፡ ኪሱ ተከፈተ፡፡ መጨረሻ የተጫነችው በግ ነስር በነስር ሆናለች፡፡ 

ጭንቅላቷን ወደሰማይ ቀና አድርገህ ያዝላት!” አልነው፡፡ እንደተባለው አደረገ፡፡ 

የበጓ ባሉካሶፍት ! ሶፍት! እባካችሁን ሶፍት . . .” አለ ብለን አስወራን፡፡ ነገሩ ካለፈ በኋላ፡፡ 

በወቅቱ አቅማችን የፈቀደው የመጀመሪያ ርዳታ ተረብ ነበር፡፡ የህክምና ጉዳይ የማይታሰብ በመሆኑ . . . እንደ ሻንጣ አንጠልጥሎ ወደ ቤቱ ሮጠ፡፡ 

በረንዳ ላይ ታስራ ለመጮህ ያልታደለችው በግ በበአል ዋዜማ ትባረካለች፡፡እንዳለው ሼክስፒር /ለአባባሉ ክብደት ልስጠው ብዬ ነው/ እንዲሁም ሆነ፡፡ 

ፍተላ 3- (በቢሆን የተፈተለ . . . የበዓል ትርርብ ላይ የተፈጠረ)

ቀጭን ድምፅ ያለው ወዳጃችን ፍየል ገዛ፡፡ ፍየሏ ስትጮህ የሰው ስም የምትጠራ ነው የምትመስለው፡፡በቀለ!” የምትል፡፡ ደግሞም እንደዛ ነው የምትለው፡፡ ቤቱ ወስዶ አሰራት፡፡ መጮህ ጀመረች፡፡ በቀጭን ድምጿ፡፡

በቀለ! በቀለ! በቀለ!”

በሩ ተንኳኳ፡፡ ባለ ፍየል ጓደኛችን በሩን ከፈተ፡፡ ጎረቤቱ አቶ በቀለ ከደጅ ቆመው፡-

አቤት ! ጠራኸኝ??”

በቀጭን ድምፁ ኧረ እኔ አልጠራሁዎትምአለ፡፡ እንዳልጠራቸው በመኃላ አረጋገጠ፡፡

እንዲህ እያሉ ሄዱ፣የማርያም ብቅል እየፈጨሁ ነው!” 

እሱ በተራው አፀፋ ተረብ ሰነዘረ፡፡

ኄኖክ ከጩኸት ይልቅ ፉጨት የሚቀናት ዶሮ ገዛ፡፡ ሊያርዳት ሲልቆቆቆቆቆይ . . . “ቆቆቆቆቆይ . . .!” ስትል የሰሙ እናቱ ለዶሮዋ አዝነው አልያም ዶሮዋ እያጣጣረች እንደሆነ ተረድተው፡-

ምነው ኄኖክ! ቆይ እያለችህ ልታርዳት!?! ”

እና ምን ላድርጋት??”

ትንሽ ከታገስክ መሞቷ ስለማይቀር ያኔ ትቀብራታለህ፡፡

ማክሰኞ 8 ኤፕሪል 2014

“ወፍ እና ማለዳ” ነጠላ ግጥም ዳሰሳ - በአብደላ ዕዝራ

ወፍ እና ማለዳ

እንኳንስ ችግኙ፥ ሰዎች የተከሉት
ሥር ይዝ ነበረ፥ አዕዋፍ የዘሩት።
ዘንድሮ ግን ወፎች፥ እንኳንስ ሊዘሩ
ናፍቆኛል ማለዳ፥ መስማት ሲዘምሩ።
ወፎች ከማለዳ-
በምን ተቃቃሩ?!
ፅልመቱ ሲገፈፍ-
እንዳላበሰሩ፤
ማዜም ተስኗቸዉ-
ተዘግቶ ጀንበሩ
ወደሚነጋበት-
ወዴትስ በረሩ?!

-----------------------------------------------------
ምንጭ = -ሞት [የግጥሞች ስብስብ]
ኄኖክ ስጦታዉ
--------------------------------------------------------------
[ ገጣሚ ኄኖክ ስጦታዉ የግጥም ስብስብ መፅሀፉን ሁለት ሶስቴ... ሊያሳትም ሲችል፥ በነፃ ሁላችንም እንድንመሰጥበት በድረ ገፁ ለቆታል። ገንዘብ እያስፈለገዉ ለሥነፅሁፍ ፍቅርና ልክፈት ማደሩን አስቀደመ። -ሞት በጥሞና ለመነበብና ለማወያየት ጥበባዊ አቅም የቋጠረ መፅሃፍ ነዉ። ለጊዜዉ አንድ ዘለላ የተዋጣ ግጥሙን አብረን share በማድረግ በመጠኑ እናንብብ። የምስጋና ያክል ነዉና - አብደላ ዕዝራ ]
---------------------------------------------------------------------------

<ወፍ እና ማለዳ> አጭር እምቅ ተራኪ ግጥም ነዉ። ትረካዉ እንደ ማዉጋት የሚወረዛ ሳይሆን ገጣሚዉን ለመዘመዘ ጉዳይ መተንፈሻና ማዉጠንጠኛ ሆነ። የርዕሱ ስክነት ፈጠጠ እንጂ ጉጉት አልቀሰቀሰም። ርዕሱ ግጥሙ ዉስጥ ባደፈጠዉ ስንኝ በተተካ ያሰኛል፤ <ወፎች ከማለዳ በምን ተቃቃሩ?> የሚነሰንሰዉ አሻሚነት የሚከሶክስ፤ ከመነሻዉ በዉስጠምት -rhythm- የሚያባንን በሆነ። ተናጋሪዉ (persona) - የወንድም የሴትም አንደበት ሊሆን ይችላል - የቆረቆረዉ፥ ያሳሰበዉ የመምከን አባዜ አለ፤ እንዴት ሳይሆን ለምን በበለጠ ያብሰከስከዋል።

ደበበ ሠይፉ <ወፊቱ> በሚለዉ ግጥሙ ቀን-ቀን አየሩን እየቀዘፈች አድማስ ሳይወስናት የቦረቀች ወፍ፥ ለአይን ያዝ ሲያደርግ መድናገሯን ተቀኘበት።

ኧረ ምን መለሰሽ ?
ወደኋላ ያዘሽ ?
መሸት ከማለቱ ያደነቃቀፈሽ ?
ወፊቱ በሌሊት ምን ይሆን ታስቢ
እኔኑ መሰልሽኝ ጐጆሽ ስትገቢ።

ደበበ የተናጋሪዉንና የወፊቱን የጓዳ ህይወት ቅዝቃዜ፥ የብቸኝነት ወጥመድ ... ህዋና የአራት ግድግዳ ስፋትና ጥበት የተወሳሰበበት ሥነልቦናዊና ኑሮዋዊ ጣጣ አነፃፀረ። ሄኖክ ግን ጐህ ሲቀድ ይህች ወፍ የማለዳ ብርቅነቷ ነዉ የረበሸዉ። መዝሙሯን፥ የአዲስ ቀን ምስራቿን እንዴት ነፈገችን ? ይቅርና እንደ ድምፅ ለእህልም -ወፍ ዘራሽ- ትበቃ የነበረዉ ከማለዳ ጋር ለምን ተቃቃሩ ? ቅኔያዊ፥ ዘይቤያዊ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ሥር ከሰደደ ሥጋት ተፋትጐ የተቀጣጠለ ዕንቆቅልሽም ነዉ::

እንኳንስ ችግኙ፥ ሰዎች የተከሉት
ሥር ይዝ ነበረ፥ አዕዋፍ የዘሩት።

ዛሬ ግን የአማርኛዉ ፈሊጥወፍ ዘራሽብሎምገና ወፍ ሳይንጫጫምን አደበዘዘዉ ? ገጣሚዉ ቃላት ሳይከምር፥ እንደ ዘገባ ፊት ለፊት እሳቦቱን ሳይዘረግፍ ሰወኛ ዘይቤን በማጠላለፍ ዕምቅ ግጥም አስነብቦናል። በአርምሞ የአካባቢዉን ቁሳዊና ህሊናዊ ዐዉድ ከቃኘና ከታከከ በኋላ ጥያቄና ግርምታ ያደነደነዉን ስንኝ ያቀብለናል፤ ስናስብበት የተዳፈነዉ ረመጥ ፋታ አያዉቅም።

ማዜም ተስኗቸዉ-
ተዘግቶ ጀንበሩ
ወደሚነጋበት-
ወዴትስ በረሩ?!

እኛ ዘንድ መንጋት አቆመ ወይ ? ሰፈራችን ህይወታችን ለጨለማ ገብሮ፥ ለብርሃን ሽንቁር እስከመቼ አቴቴ ቢስ እንሆናለን ? ወፎች ጐህ ወደ ቋጠረዉ ተሰደዉ፥ ጀንበር እንደ ጣራ ተደፍኖ ሲቀር፥ ስጋቱ ያዉካል።ጀምበር ካለ እሩጥ፥ አባት ካለ አጊጥእንደ ቅዠት ሊፈረካከስ ? ተስፋ ላለመቁረጥ የሄኖክ ግጥም ጀርባ እንዳለዉ ማወቅ ሊኖርብን ነዉ። የግጥሙን ተናጋሪ መጠራጠር እንጀምራለን፤ ቀን-ቀን እያንቀላፋ ለወፍ ዜማና ለንጋት መፍካት የሚቀሰቅሰዉስ ካጣ ? ይህንን ሄኖክ በሌላ ባለአንድ አንጓ ግጥሙ < ታሽጓል> የሚለዉን ግለሰብ ይገረምማል። እንዴት ከግሉ ደጃፍ ተገትሮ የራሱን በር ያንኳኳል ? የአደባባይ ሳይሆን ከዉስጡ የተጋረደዉ ንጋት ይብሳል።

ቢጠሩት ላይሰማ፥
ልቤ ተጠርቅሞ
የሚያንኳኳዉ ማንነዉ፥
ደጃፉ ላይ ቆሞ ?!

ይህ ግለሰብ ብንን ሲል፥ በወፍና ንጋት ልክፈት ተቀንብቦ ፍለጋዉን አይገታም። እያደባ የደረሰባት ወፍ ግን < ጉጉት> ሆና ታሸማቅቃለች።

ከእርግቦች መሐል፥
እርግብ ተመስላ፤
እርግብ ናት
ያልናቱ፥
ላባ ተከልላ፤
ሥትከፍተዉ አፏን፥
አየን ጥርስ አብቅላ።

ያቺ የምትዘምረዉ፥ ጨለማን ተርትሮ ብርሃን ሲያንሰራራ የሚያቅበዘብዛት ወፍ ሲያልም ይኑር፥ ወይስ ተስፋን እያማሰለ እያቦካ የህይወት በገናውን እየቃኘ የግሉን ዜማ ያፈልቅ የሆን ? የግጥሙ ጥንካሬ አለማብቃቱ። ይህን ንባብ በህዝብ ቅኔ - መንፈስ ለማርገብ ያክል - እንቋጨዉ። ፀሐይ የተባዕት መጠሪያ ሆኖ እንደ ሰምና ወርቅ ቢዳዳዉም፥ ለሄኖክ < ወፍ እና ማለዳ > ማንፀሪያም ነዉ። ማለዳ የናፈቀን ያህል፥ ፀሐይ የሚፈታተናትም ሄዋን ታቃስታለች።

በሐምሌ በነሀሴ እንድያ ስዋትት
እንዴት በመስከረም በፀሐይ ልሙት ?


****************************************