2012 ኖቬምበር 29, ሐሙስ

ፍቅር ጥላ ሲጥል በ-ገብረ ክርስቶስ ደስታ


ፍቅር ጥላ ሲጥል

በገና
ቢቃኙ፡
ሸክላ
ቢያዘፍኑ
ክራር
ቢጫወቱ፡
ለሚወዱት
ምነው
ሙዚቃ
ቢመቱ
ቢቀኙ
ቢያዜሙ
ቃል
ቢደረድሩ
ጌጥ
ውበት
ቢፈጥሩ
ቤት
ንብረት
ቢሠሩ
አበባ
ቢልኩ
ደብዳቤ
ቢልኩ
ምነው ______
ቢናፍቁ !
አገር
ቢያቋርጡ ______
ቢሔዱ
ቢርቁ
ዓመት
ቢጠብቁ
ዘመን
ቢጠብቁ።
ለሚወዱት ምነው ....

ገብረ ክርስቶስ ደስታ

1998 96-97


1 አስተያየት:

  1. እኔ እማልሰጣችሁ ፣ እናንተ እማትወስዱት….
    ምድር ሰማይ ሆኖ፣ ሰማይ ቢሆን ምድር፣ ቢፋለስ ተፈጥሮ
    በጨረቃ ቦታ፣ ብትወጣ ጸሀይ፣ ዘመን ተቀይሮ፤
    ቢተባበራችሁ፣ የዓለም ኃይል በአንድነት
    እኔ እማልሰጣችሁ፣ እናንተ እማትወስዱት፤……
    የሰው ልጅነቴን፣ ኢትዮጵያዊነቴን!
    አረንጓዴ - ቢጫ - ቀይ፣ ሰንደቅ ዓላማዬን!
    ከዓምላክ ያገኘሁት፣ ፍጹም ነጻነቴን!
    -----//----
    ፊልጶስ/ ግንቦት 2005

    ምላሽ ይስጡሰርዝ