2012 ኦክቶበር 26, ዓርብ

"ችግሬ" :- የብሌን ከበደ ግጥም



ችግሬ

እርም ያባቴን ሥጋ

ለዓለም ብተጋ

ዓለም በቃኝ ብዬ
ላልመለስ ምዬ
ምዬ ተገዝቼ
ላልመለስ ዝቼ
ሁሉን ነገር ትቼ
አንተንም 'ረስቼ
ይዤ ጾም ጸሎቴን
ውዳሴ ስግደቴን
ልመንን እልና
ታስገድፈኛለህ በ'ልሜ ትመጣና::

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ