አንዳንዴ፣ ራሴን እንዲህ ስል እጠይቀዋለሁ፦
ሰፊውን አለም ማን አጠበበው?
እውነት ጀግና ማለት ለአገሩ የሞተ ነው? የገደለ?
ለአገር መሞት ማለት፣ በሌላው መገደል ብቻ ነው? ወይስ መግደል?
የመሞት ዓላማው ከመግደል በመጠኑም ቢለይም ስንኳን ፣ ሰውን ያክል አምሳያ መግደል በርግጥ ጀግነት ነው? ወይስ አረመኔነት? ወይስ ተፈጥሯዊ የሆነ የማንነት መገለጫ?!
ለአገር መሞት ነው ጀግንነት? ወይስ ፣ በሰው መገደል ነው ጀግንነት?!
እራሱ «ጀግንነት» ምንድነው?!
ክብር ነው?
ስሜት ነው ?
ወይስ
ሌላ?
ጀግና ማለት፣ ላመነበት አላማ የተገደለ ነው?! ወይስ… የገደለ?!
ገድሎ የሞተው ፣ ሞቶ ካሸነፈው የሚለየው በምንድነው?
በሕይወት?
በሞት?
በድል?
በሽንፈት?
. .
.
.
.
.
.
.
.
. .
ከጦርነቱ የተረፈ በርግጥ ጀግና ነው ?!
.
.
በርግጥ የቱ ነው ጠባብ?!
አገር ከዓለም ይጠባል?!
ዓለም ከአገር ይሰፋል?!
አስፍቶ ለተመለከተው በርግጥ ዓለም የአገር አካል ናት? ወይስ
ዓለም ከሰፈር ትጠባለች?!
እናም፣ ጥያቄው ማብቂያ የለውም። መልሱ ግን ይብሳል¡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ