ሐሙስ 8 ኖቬምበር 2012

ጥቂት ፍልስፍና ከ (ዘገብረየሱስ)


ጥቂት ፍልስፍና
ቅዱስ መፀሐፍ ፣ ፈጣሪ ለ አዳም አጋር ትሆነው ዘንድ ሔዋንን ሲፈጥርልት ፣ አዳምን በከባድ እንቅልፍ ጥሎት ነው ብሎ ያስተምራል። ዛድያ እኔ ደግሞ ትንሽ ተመራመርኩ። የ አዳም ከባድ እንቅልፍ ፣ ምን ይሆን ብዬ? ተያ ተመራምሬ ሳበቃ ፣ የ አዳም እንቅልፍ ለኔ ምነው ብዬ ራሴን ጠየቅኩት? ጠይቄም ፣ መልስ አገኘሁ። እንዲህ የሚል። አዳም ከእንቅልፍ ነቃ ፣ ሄዋንንም ከጎኑ አገኘ ፣ አጋርም ሆነቸው እናም ኑሮን አብረው ኖሩ። አብረው ተደስቱ ተዋረዱ ። ወልዱ ከበዱ። አብረውም ከፈጣሪ ምህረት አገኙ( እዚህ ላይ ግን ፣ ለ አዳም ቃል ገባለት እንጂ ፣ ስለ ሔዋን የተጠቀሰ ነገር ትዝ አይለኝም። ግን አንድም ሆነው የለም ፣ የአዳም የሆነው ፣ የሄዋን ነው ፣ የሔዋንም የ አዳም)። ወደኔ መለስኳት። የኔ እንቅልፍ አልኩኝ ፣ በልጅነቴ የኖርኩት እድሜ ነው። ወላጆች እንቅፋት እንዳይመታኝ ፣ እንዳይርበኝ እንዳይጠማኝ ፣ ሲያሳድጉኝ ፣ ያሳለፍኩት እድሜ። እናም ከዛ የእንቅልፍ እድሜ ስነቃ ፣ እና አይኖቼን ስገልጥ ፣ መጀመርያ ፣ የየኋትን ሔዋን ፣ ሔዋኔ ነች ብዬ አልኩ። እዚህ ላይ ፣ እንዴት አወቅክ ካላችሁ ፣ አዳምም ምርጫ አልነበርዉም። ከጎኑ ያገኛትን ተቀበለ እንጂ። እኔም እንደዛው። ከዛ ጥቂት መስመር ፣ ግጥም ሞነጨርኩኝ። እነሆ ጀባ ፣ (ይህ የኔ ፍልስፍና እንጂ ፣ የማንም አስተምህሮ አይደለም ፣ ስለጥቅ ደግሞ ፣ እኔ ግጥሜን ለማስደገፍ የተጠቀምኩት ፣ ሚዛን ነው ልበል ፣ እንጃ )
*ሔዋን*
ለብቻህ ስትኖር ፣
...........ሌቱን ስትገፋ
............ከምትርቅህ ተስፋ
ብሎ አስተዉሎ
........አጋር ለኔው ሰራ
እኔን በእንቅልፍ ጥሎ
..................ከአካሌ ከፍሎ
አፈጣጠርሽን ሳላዬው ቀርቼ
ጌታዬ ሲሰራሽ ፣ እንቅልፌን ተኝቼ
ድንገት ዛሬ ነግቶ ፣ ከእንቅልፌ ስንቃ
አጋር ጎን አጥንቴን ፣ ባያት ጎኔ ወድቃ
አፍ ፈታሁ በስሟ ፣ ገፅዋ ፊደል ሆኖ
ፍቅር ተማርኩ ከልቧ ፣ ልቤ ለርሷ መንኖ
እሱም አያስተኛኝ ፣ እኔን በእንቅልፍ ጥሎ
ሌላ አጋር አይስራ ፣ ከጎኔ ገንጥሎ
አንች ነሽ ብያለሁ ፣ የጎኔ ጎዶሎ

(ዘገብረየሱስ ጥቅምት 20-2005)

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ