“ዶሮዋ
መንገዱን አቋረጠች” እንደሚለው ሁሉ “ሁለት ላሞች አሉህ” በሚለውም ብዙ ተፈትሏል፡፡ የሁለቱ ላሞች ታሪክ ሽሙጣዊ መልዕክት በማሕበራዊ፣ አኢኮኖሚና ሃይማኖት ዙሪያ የሃሳብ ማስተላለፊያነት ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ እኔም ለዛሬ በሁለቱ ላሞች ሰበብ ከተነገሩ አያሌ ሽሙጦች መካከል ጥቂቶቹን ላካፍላችሁ፡፡
በአንድ
ወቅት የሩሲያ ማፊያዎችን ፍራቻ ንብረታቸውን እንዳይታወቅ ሲሉ ያላቸውን ስለሚደብቁ ሰዎች በአሽሙር መልክ እንዲህ ተብሎ ነበር፡፡ “ሁለት ላሞች አሉህ፡፡ ጥቂት ቮድካ ጠጣና ደግመህ ቁጠራቸው፡፡ ያኔ አምስት ላሞች ይኖሩሃል፡፡”
በፋሺዝም
ዕይታ የሁለት ላሞችህ ዕጣ በሜታፎር እንዲህ ተብሎ ነበር፡፡ “ሁለት ላሞች ካሉህ ሁለቱንም ለመንግስት ስጥ፡፡ መንግስትም ጥቂት ወተት ይሸጥልሃል፡፡”
በሶሻሊዝም
ሁለት ላሞች ቢኖሩህ መንግስት አንዱን ካንተ ተቀብሎ ለጎረቤትህ ይሰጠዋል፡፡ በኮሚኒዝም ግን ሁለቱንም ላሞችህን ለመንግስት ሰጥተህ ጥቂት ወተት ብቻ ትቀበላለህ ተብሎም ነበር፡፡
የሁለት
ላሞች አሉህ ፍተላ በዲሞክራሲ ዕይታ ምን እንደሚመስልም ተቃኝቷል፡፡ የአሜሪካ ዲሞክራሲ “ሁለት ላሞች ካሉህ አሁን ጎረቤትህ የሚጠጣውን ወተት ከማን ማግኘት እንዳለበት መወሰን ይችላል፡፡” በሕንድ ዲሞክራሲ “ሁለት ላሞች ቢኖሩህ ልታመልካቸው መብት አለህ፡፡” በአንባገነን መንግስት ግን የሁለት ላሞችህ መኖር ሌላ ገፅታ አለው፡፡ “ሁለት ላሞች ካሉህ ፣ ሁለቱንም ነጥቆ አንተን ይገድልጋል፡፡”
ካፒታሊዝም
የተፈተለው የሁለት ላሞች አሽሙር ደግሞ ይህን ይመስላል፡፡ “ሁለት ላሞች ካሉህ፣ አንዷን ሸጠህ ኮርማ ግዛ፡፡”
ኢትዮጵያስ
ከሁለቱ ላሞች አንግል ምን ትመስል ይሆን ?
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ